አትሳቅ አትበሉኝ - በምንተስኖት መንገሻ

መታሰቢያነቱ ለጫማ አልባው ብላቴና ይሁንልኝ

Young child carrying bags, Agere Maryam, Ethiopia.jpg

A young child carrying bags, Agere Maryam, Ethiopia. Credit: DeAgostini/Getty Images

ጭጋግ መሬት ቢረግጥ

ጸሃይ ብትሸፈን፣

አየሩ ቢታፈን፣

ኑሮ ረመጥ ቢሆን፣

ዙሪያው ገባው ሁሉ

ማቅ ለብሶ ቢዳፈን፡፡

ሳቄን ማን ከልክሎኝ፣

አልፎ ሂያጂነቴን

ጉዞዬን ማን ገቶኝ፣

እርቃኔንም ብሆን

የውስጤን ነጻነት እንደያዝኩት አለሁ

በውስጤ ሃብት አለኝ፡፡

አትሳቅ አትበሉኝ ... ሳቄ  የቀረ ዕለት፣

የደኸየሁ  እንደሁ ... በፈገግታ ንፍገት፣

ያኔ ነው የኔ ሞት፡፡

ጫማም አላቂ ነው

ከስር ተሸንቁሮ፣

ልብስም ይቀደዳል

ውሉ ተተርትሮ፣

ሁሉም አላፊ ነው

ያረጃል ያፈጃል

ትናንትም አርጅቶ

ጥንት ይባላል ዱሮ፡፡

አትሳቅ አትበሉኝ  ... ሳቄ  የቀረ ዕለት

የደኸየሁ  አንደሁ ... በፈገግታ ንፍገት፣

ያኔ ነው የኔ ሞት፡፡

.............................

ጸደይ 2020


1 min read

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS



Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now