የብር ኖቶች ለውጥ በኢትዮጵያ

*** የብር ኖቶቹን ለምን መቀየር አስፈለገ ?

New Birr Notes

Source: PMOE

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነባሮቹን የ10 ፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ የሁለት መቶ ብር ኖትን ወደ ሥራ ታስገባለች።

የ5 ብር ገንዘብ ባለበት ቀጥሎ፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ሣንቲም የሚለወጥ ይሆናል።

የብር ኖቶቹን ለምን መቀየር አስፈለገ ?

- መደበኛ ባልሆነ መንገድ እንዲሁም ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ የሚዘዋወረውን ገንዘብ ለመሰብሰብ ፣

- ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ፣

- ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ ለማስቀረት ፣

እርምጃው የፋይናንስ ተቋማት የገንዘብ እጥረትን ለመቋቋም እንዲችሉም እንደሚያግዝ ከPMO ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አሁን በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ?

አብዛኛው የሕትመት ሥራ ተገባዶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግምጃ ቤት ይገኛል። የስርጭት ስርዓት እና ዕቅድ የተዘጋጀ ሲሆን ፣ በሚመለከታቸው አካላት አማካኝነት ይተገበራል።

በገንዘብ ቅያሬው ሂደት ውስጥ የጸጥታ አስከባሪ አካላት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን ፣ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ከማኅበረሰቡ ጋር በመተባበር ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ያስፈጽማሉ ተብሏል።

ከብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት ፣ ከብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከፌደራል ፖሊስ የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ፣ ሂደቱን በበላይነት ያስተባብራል።

የክልል መንግሥታትም ተመሳሳይ ኮማንድ ፖስት አቋቁመው ሥራውን እንዲያከናውኑ ይጠበቃል።

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ብቲዊተር ገፃቸው ከፃፉትና ከጠ/ሚ ጽ/ቤት የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት


Share

Published

By Stringer Report

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
የብር ኖቶች ለውጥ በኢትዮጵያ | SBS Amharic