ኦሚኮርን በአለም አቀፍ ዙሪያ የሆስፒታል አገልግሎት እንዲስተጓጎል አደረገ

በአሜሪካ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች በአንድ ቀን ብቻ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን ፤ ቁጥሩም የአለማችን ከፍተኛው አንደሆነ ተነግሮለታል ።

German chancellor Olaf Scholz (AAP)

Olaf Scholz has taken office as the German chancellor. Source: Getty Images

በአለም አቀፍ ዙሪያ የሚገኙ ሆስፒታሎች የኦሚኮርን መስፋፋት ተከትሎ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ናቸው ተባለ ።

የመስኩ ባለሙያዎች እንዲሚናገሩት ከሆነ የተጨማሪ ማጠናከሪያ ከትባት (ቡስተር) ፤ ሆስፒታል ሊገቡ የሚችሉ ህሙማንን ቁጥር በመቀንስ ረገድ ያለው አስተዋትጻኦ ከፈፍኛ መሆኑን ነው ። አያይዘውም ተጨማሪ የቫይረስ አይነቶች እንደሚመጡም መጠበቅ ግድ ነው ብለዋል ።

እንግሊዘ ወደ ጠንካራው ብርዳማ ወቅት እይሄደች ባለችበት እና የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች በጨመሩብት ወቅት ፤ በአንጻሩ የማቾች ቁጥን ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር እጅግ ዝቅ ያለ ነው። ይህም የክትባቱን ውጤታማነት አንዱ ማሳያ ነው ተብሏል።

ለንደን በሚገኘው በሮያል ፍሪ ሆስፒታል  ከፍተኛ እንክብካቤ የሚያሻቸው ህሙማን በሚቆዩበት ክፍል ውስጥ ካሉ የኮሮናቫይረስ ህሙማን መካከል ግማሽ ያህሉ ሁለቱን ክትባቶች ያልወሰዱ ናቸው።

በአሁን ሰአትም 19,000 የሚሆኑ የኮቪድ-19 ህሙማን ሲኖሩ ፤  ባላፈው የሪፕርት ወቅት ላይ 398 ሰዎች ህይወታቸውም ማጣታሽቸው ተገልጿል ።

በተያያዥም በፈረንሳይ በዚህ ሳምንት በአንድ ቀን ብቻ 368,000 ስዎች መያዛቸው የተገለጸ ሲሆን ፤  በጣልያን ባለፈው ማክሰኞ 220,532  ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ።

የጀርመኑ ቻንስለር አህላፍ ሾልዝ በፓርላማ ንግግራቸው የኮቪድ-19 በመላው አገሪቱ በግዴታ መውሰድ እንዳለበት ተናግረዋል። በጀርመ  83፣430 አዲስ የኮቪድ ተያዦችን ቁጥር ተመዝግቧል  ።

በአሜሪካ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች በአንድ ቀን ብቻ በኮሮናቫይረስ  የተያዙ ሲሆን ፤ ቁጥሩም የአለማችን ከፍተኛው አንደሆነ ተነግሮለታል

ይህ በእንዲህ እንዳለ የመስኩ ሳይንቲስቶች ኦሚኮርን ቫርያንት የመጨርሻው አይነት ቫይረስ እንደማይሆን እና ሌሎችም ተጨማሪ የቫይረስ አይነቶች ሊመጡ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል ።

 


Share

Published

Updated

Presented by Martha Tsegaw
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
ኦሚኮርን በአለም አቀፍ ዙሪያ የሆስፒታል አገልግሎት እንዲስተጓጎል አደረገ | SBS Amharic