በዚህ ዓመት አንዱ የላቀ ስሜት ቢኖር ምስጋና ነው።
ይህ ዓመት ለማናችንም ቀላል አልነበረም።
የተወሰንነው ዘመዶቻችንን አጥተናል። ሌሎቻችን ሥራዎቻችንና መተዳደሪያችንን አጥተናል። ከቤተሰባችን ተለያይተናል፤ በገደቦቹ ወቅት ተገልለናል እንዲሁም ከምናፈቅራቸው ዳር መታደም ተስኖናል።
ለሁላችንም ይህ ዓመት የጭንቀትና በእጅጉ እርግጠኛ ያልሆንበት ጊዜ ነበር።
ይሁንና በውስጡ አልፈናል፤ ዳግም አንዳችን ካንዳችን በጋራ ተሰባስበናል።
አውስትራሊያውያን ድንቅ መንፈስ ያላቸው ድንቅ ሰዎች ናቸው። በዚህም ዓመት የአውስትራሊያውያን መንፈስ ዳግም ብሩኅ ሆኖ ፈንጥቋል።
ይሁንና ማኅበራዊ መራራቅ አድርገን፣ አንዳችን ካንዳችን ጋር በስሜት መቆራኘት ነበረብን።
ጥቁሩን በጋ እንድንወጣ ያደረጉን የእሳት አደጋ ተከላካዮችና በጎ ፈቃደኞች ነበሩ።
በሺህ ወረርሽኝም ወቅት ሐኪሞችና ነርሶች፣ ተመራማሪዎችና ሳይንቲስቶች ለኛ ጥበቃና ክብካቤ የላቀ ግብር ተግብረዋል።
የችርቻሮ ሠራተኞች የአቅርቦት ሰንሰለቱ እንዲቀጥል አስችለዋል።
በጎ ፈቃደኞች ማንም ሰው ወደ ኋላ እንዳይተው ወይም አለማንም እንዳይቀር አድርገዋል።
የመንግሥት ሠራተኞች በመላ አገሪቱ ተሰማርተው ለሕዝብ ድጋፍን አከናውነዋል።
ሁሉም የየራሱን ድርሻ በመወጣት።
አሁን እንኳ ሲድኒ ውስጥ በሰሜናዊ ባሕር ዳርቻ ሁሉም የየድርሻውን እየከወነ ነው፤ በመላ አገሪቱ ያለነው ደህንነታችን እንዲጠበቅ።
አውስትራሊያ ውስጥ የትም ሁኑ የት፣ በዚህ የገና በዓል እንደ አውስትራሊያውያን ዳግም በበረከተ ጸጋችን እንደ አገር እንተማመናለን።
እናም በአውስትራሊያዊ ዘይቤያችን በተቻለን መጠን ሁሉ እኒህን በረከተ ጸጋችንን ዳግም ሳናመነታ እንጋራለን።
በዚህ ዓመት በዓለ ገናችን ምስጋናን እናቀርባለን፤ ስለምን ከፈተናዎችቻንን ይልቅ በረከታችን ያመዝናልና።
ለሁላችንም፤ ክርስቲያን ለሆንነውም ሆነ ላልሆንነው ሁሉ ይህ የገና በዓል የታላቅ ተስፋ ጊዜ ነው።
በዚህ በዓለ ገና ለአውስትራሊያ ጸሎቴ ከታላቁ ጥቅስ “መልካም ከማድረግ አንታክት። ተስፋ ካልቆረጥን በወቅቱ ከምርቱ እናጭዳለንና” የመነጨ ነው።
በደህና ቆዩ፤ ከኮቨድ ተጠብቃችሁ ቆዩ።
እግዚአብሔር በዚህ በዓለ ገና እናንተንና ቤተሰባችሁን ይባርክ።
መልካም የገና በዓል፤ አውስትራሊያ
ስኮት ሞሪሰን
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር