የደቡብ አውስትራሊያ አዲስ የኮሮናቫይረስ ገደቦች

*** ደቡብ አውስትራሊያ ውስጥ ከኖቬምበር 19 ጀምሮ ቢያንስ ለሚቀጥሉት ስድስት ቀናት የአገልግሎት ተቋማት ዝግ ይሆናሉ

SA COVID-19

South Australia's chief public health officer Nicola Spurrier Source: AAP

ደቡብ አውስትራሊያ ውስጥ ከኖቬምበር 19 ጀምሮ ቢያንስ ለሚቀጥሉት ስድስት ቀናት የአገልግሎት ተቋማት በሙሉ ዝግ ይሆናሉ፡፡

ይህንንም እርምጃ ተከተሎ ለ8 ቀናት የሚቀመጥ ከፊል ገደብ ይኖራል፡፡

ሁሉም ሰው በቤቱ መቀመጥ ይኖርበታል ( አስፈላጊ በሚባሉ ተቋማት ከሚሰሩት በቀር)

ከአንድ ቤተሰብ አባል አንደ ሰው ብቻ ለምግብ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን በቀን አንድ ጊዜ  ወጥቶ መገብየት ይቻላል

  • ትምህርት ቤቶች እና ሙአለ ህጻናት ፦ ከኖቬምበር 19 ጀምሮ ዝግ የሚሆኑ ሲሆን ፤ በመኖሪያ ቤታቸው መቆየት ለአደጋ ከሚያጋልጣቸው ተመሪዎች እና ወላጆቻቸው አስፈላጊ ተቋማት በሚባሉት ውስጥ ከሚሰሩት ልጆች በቀር ሁሉም በቤት ይቆያሉ
  • ዮኒቨርሲቲዎች፦ ከኖቬምበር 19 ጀምሮ ዝግ ይሆናሉ
  • በውጭ የሚደረጉ ሁሉም አይነት  የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች እና ስፖርቶች ተከልክለዋል
  • የአረጋውያን መጦሪያዎች እና የአካል ጉዳተኞች መንካባከቢያ ስፍራዎች ህይወታቸው ለማለፍ ጥቂት ቀናት የቀራቸውን ሰዎችን ብቻ እንዲጎበኙ ይፈቅዳሉ
  • ሁሉም የምግብ እና መጠጥ አቅራቢዎች ፤ ምግብን ገዝተው የሚሄዱባቸውን ጨምሮ ሁሉም የምግብ አዳራሾች ዝግ ይሆናሉ
  • በምርጫ የሚደረጉ የቀዶ ጥገና ህክምናዎች  የተሸጋገሩ ሲሆን ፤ የካንሰር እና ድንገተኛ ቀዶ ጥገናዎች በተለመደው ሁኔታ ይከናወናሉ
  • የገበያ መደብሮች እና የመጠጥ መሸጫዎች ክፍት እንደሆኑ ይቆያሉ
  • የህክምና ተቋማት ፤ የአእምሮ ጤና አገልግሎት ሰጪዎች ፤ የእንስሳት ሃኪም ቤቶች ክፍት ይሆናሉ ፤
  • የህዝብ መጓጓዣዎች ፤ አየር ማረፊያዎች ፤ ባንክ ፤ ፖስታ ቤት እና የነዳጅ ማደያዎች ክፍት እንደሆኑ ይቆያሉ ፡፡

Share

Published

By Martha Tsegaw

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service