Rural landscape, Western Australia, Australia
Rural landscape, Western Australia, Australia

የአውስትራሊያ ብሔራዊ መዝሙርና የዜግነት ቃል ኪዳን በእርስዎ ቋንቋ

የአውስትራሊያ ብሔራዊ መዝሙር እና የዜግነት ቃል ኪዳንን በመላው አውስትራሊያ በሚነገሩ በርካታ ቋንቋዎች መልሰን ተርጉመናል።

Published

By Kassahun Negewo
Source: SBS
SBS በመላ አውስትራሊያ ውስጥ ያሉ የአቦርጂናል እና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎችን በልማዳዊ የሀገር ባለቤትነትና ከመሬት፣ ውኃና ማኅበረሰብ ጋር ስላላቸው ያልተቋረጠ ቁርኝት ዕውቅናን ይቸራል።

የAdvance Australia Fair የመጀመሪያ ሥነ ግጥሞች የተፃፉት በ1878 በአውስትራሊያ መምህርና የዜማ ደራሲ ፒተር ዶድስ ማኮርሚክ ነው። ዝማሬው ኤፕሪል 19 ቀን 1984 በአውስትራሊያ ብሔራዊ መዝሙርነት ይሁንታን አግኝቷል።

እ.ኤ.አ. በ2021 በመዝሙሩ ሁለተኛ መስመር ውስጥ ያሉት ቃላቶች ከ'ወጣት እና ነፃ' ወደ 'አንድ እና ነፃ' ተሻሽለዋል፤ አካታችነትን ለማንፀባረቅ።

መዝሙሩ በይፋዊ ክብረ በዓሎች፣ ስፖርታዊ ውድድሮች እና ሌሎች የማኅበረሰብ ዝግጅቶች ላይ ይዘመራል።
የአውስትራሊያ ብሔራዊ መዝሙር ስንኞች


አውስትራሊያውያን ሁላችንም ደስ ይበለን፣

ነፃ እና አንድ ለሆን ነው፤

ለልፋታችን ወርቃማ አፈር እና ሀብት አለን፤

ሀገራችን በባሕር የተከበበች ናት፤

ምድራችን በተፈጥሮ ፀጋዎች የተሞላች ናት

ውበታችን፣ የከበረና ብርቅ ነው፤

በታሪክ ገፅ፤ በእያንዳንዱ ምዕራፍ

አውስትራሊያን በፍትሐዊነት እናስቀድም።

ከአንፀባራቂው ደቡባዊ መስቀላችን ስር

በልብ እና እጆቻችን እንታትራለን፤

ይህችን የእኛ የጋራ ብልፅግና

በሁሉም ምድሮች ዝናን ለማላበስ፤

ለእኒህ ባሕር አቋርጠው ለመጡቱ

የምናጋራቸው ወሰን የለሽ መስኮችች አሉን፤

ሁላችንም በቁርጠኝነት እናብር

አውስትራሊያን በፍትሐዊነት ለማስቀደም

በሐሴት ስሜት እንዘምር

አውስትራሊያን በፍትሐዊነት እናስቀድም።
Australians Celebrate Australia Day As Debate Continues Over Changing The Date
- Credit: Don Arnold/Getty Images

የአውስትራሊያ ዜግነት ቃል ኪዳን

እ.ኤ.አ. በ1949 የአውስትራሊያ ዜግነት ግብር ላይ መዋል ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ ከስድስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በመደበኛ የዜግነት አሰጣጥ ሥርዓት ለዜግነት በቅተዋል።

ሴፕቴምበር 17 የሚከበረውን የአውስትራሊያ ዜግነት ቀንን አካትቶ የዜግነት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት የሚዘጋጀው በአካባቢ ምክር ቤቶች ነው።

የክብረ በዓሉ አንድ አካል ሆኖም፣ የአውስትራሊያ ብሔራዊ መዝሙር ይዘመራል፣ እናም ሰዎች የአውስትራሊያን ዜግነት ከኃላፊነቶቹ ጋር ሲቀበሉ ቃል ኪዳን ይገባሉ።

ሁለት ዓይነት ቃል ኪዳኖች አሉ፣ አንደኛው እግዚአብሔርን የሚጠቅስ ነው።

ቃል ኪዳን ዓይነት 1 

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በእግዚአብሔር ስም፣

ለአውስትራሊያ እና ሕዝቧ ልታመን ቃል ኪዳን እገባለሁ፣

የእነርሱን ዲሞክራሲያዊ እምነቶች እጋራለሁ፣

የእነርሱን መብቶችና ነፃነቶች አከብራለሁ፤ እንዲሁም

የእነርሱን ሕጎች አስጠብቃለሁ፤ እታዘዛለሁም።

ቃል ኪዳን ዓይነት 2 

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ፣

ለአውስትራሊያ እና ሕዝቧ ልታመን ቃል ኪዳን እገባለሁ፣

የእነርሱን ዲሞክራሲያዊ እምነቶች እጋራለሁ፣

የእነርሱን መብቶችና ነፃነቶች አከብራለሁ፤ እንዲሁም

የእነርሱን ሕጎች አስጠብቃለሁ፤ እታዘዛለሁም።

የአውስትራሊያን ብሔራዊ መዝሙርና የዜግነት ቃል ኪዳን በቋንቋዎ ያንብቡ፤ ያድምጡ


Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service