ቪክቶሪያ ውስጥ የተወሰኑ የኮሮናቫይረስ ገደቦች ዳግም ተጣሉ

*** የፊት ጭምብል ማጥለቅና የቤት ውስጥ የሰዎች መሰባሰብ ብዛት ላይ ለውጥ ተደርጓል

Victorian Premier Daniel Andrews.

Victorian Premier Daniel Andrews. Source: AAP

አንድ የ26 ዓመት ግራንድ ሃያት ሆቴል ወሸባ ሠራተኛ በኮሮናቫይረስ መያዝን ተከትሎ የቪክቶሪያ መንግሥት ከዛሬ ሐሙስ ፌብሪዋሪ 04 ጀምሮ የፊት ጭምብል ማጥለቅ፣ የቤት ውስጥ መሰባሰብና የሥራ መመለስ መጠንን አስመልክቶ መለስተኛ ለውጥ አድርጓል።

በዚህም መሠረት ነዋሪዎች በማናቸውም ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው ቤቶች ውስጥ (ሥራ፣ የገበያ አዳራሾች፣ ትምህርት ቤት ክፍል ውስጥ) በመሳሰሉት ሥፍራዎች የፊት ጭምብል እንዲያጠልቁ፣ ቀደም ሲል ቤት ውስጥ እስከ 30 ሰዎች ለመሰባሰብ እንዲችሉ ተፈቅዶ የነበረው ወደ 15 ዝቅ ብሏል፣ ከሰኞ ፌብሪዋሪ 8 ጀምሮ 75 ፐርሰንት ሠራተኞች ወደ ሥራ እንዲመለሱ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በቫይረስ ክስተቱ ሳቢያ ወደ 50 ፐርሰንት ዝቅ እንዲል ተደርጓል።    

በቫይረሱ የተያዘው ግለሰብ ጃኑዋሪ 29 ራስል ስትሪት ኤክስፎርድ ሆቴልን 11pm እና 11.35pm እንዲሁም ኪባብ ኪንግዝ ከ 11.24pm - 12.15am ተገኝቷል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ግለሰቡ የተገኘባቸው አካባቢ የነበሩ ግለሰቦች የኮሮናቫይረስ ምርመራ እንዲያደርጉ የተጠየቁ ሲሆን፤ እንዲሁም ግርናድ ሃያት ሆቴል የነበሩ 600 የአውስትራሊያ ኦፕን ተጫዋቾች፣ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የቫይረስ ምርመራ አድርገው ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው እስኪረጋግጥ ድረስ ራሳቸውን እንዲያገልሉ ተደርጓል።

በዛሬው ዕለት ፌብሪዋሪ 4 ሜልበርን ፓርክ ውስጥ የአውስትራሊያ ኦፕን ግጥሚያ አይካሄድም።

 


Share

Published

By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
ቪክቶሪያ ውስጥ የተወሰኑ የኮሮናቫይረስ ገደቦች ዳግም ተጣሉ | SBS Amharic