ቪክቶሪያ ላይ ተጥሎ ያለው የኮሮናቫይረስ ገደብ ከዕኩለ ለሊት በኋላ ሊነሳ ነው

*** የፊት ጭምብል ማጥለቅ ግዴታዎች ላልተዋል

SBS Amharic

Source: SBS Amharic

ከዛሬ ዓርብ ፌብሪዋሪ 26 ዕኩለ ለሊት ጀምሮ ቪክቶሪያ ላይ ተጥሎ ያለው ደረጃ ሁለት የኮሮናቫይረስ ገደብ ቅድመ የገና በዓል ወደ ነበረበት ይመለሳል። 

በዚህም መሠረት፤

ማኅበራዊ

  • ከቤት ለመውጣት ገደብ የለም
  • በአደባባይ ለመሰባሰብ ከተለያዩ የቤተሰብ አባላት እስከ 100 ሰዎች መሰባሰብ ይችላሉ (ቁጥሩ ዕድሜያቸው ከ12 ወራት በታች የሆኑ ሕጻናትን አይጨምርም) 
  • በቀን ቁጥራቸው ከ30 ያልበለጡ ሰዎች ቤትዎ መጥተው ሊጎበኝዎት ይችላሉ (ቁጥሩ ዕድሜያቸው ከ12 ወራት በታች የሆኑ ሕጻናትን አይጨምርም) የቤትዎ ጓሮ ወይም በራፍ እንደ ቤት ይቆጠራል
የፊት ጭምብሎች

  • የፊት ጭምብሎችን ማጥለቅ ግድ የሚሰኙት የሕዝብ ትራንስፖርት፣ ታክሲና ሌሎች በጋራ የሚጋሯቸው የትራንስፖርት አገልግሎቶች ሲጠቀሙ፤ የአረጋውያን መጠወሪያ ተቋማት፣ ትላልቅ የችርቻሮ ሱቆች፣ የገበያ አዳራሾችና ሱፐርማርኬቶች የመሳሰሉ የቤት ውስጥ መገበያያ ሥፍራዎች
ትምህርት ቤቶች

  • ትምህርት ቤቶች፣ ሙዋዕለ ሕጻናትና የጎልማሶች መማሪያዎች ክፍት ሆነው ይቀጥላሉ
ሥራ

  • ከ75 ፐርሰንት ያልበለጡ ሠራተኞች በየሥራ ገበታቸው መሰማራት ይችላሉ
  • ሁሉም የሥራ ሥፍራዎች የኮቨድጥንቃቄ ዕቅድ ግብር ላይ ማዋል ይጠበቅባቸዋል
የአካል እንቅስቃሴና መዝናኛዎች

  • የቤት ውስጥ የአካል እንቅስቃሴና የማኅበረሰብ ስፖርት ርቀታቸውን ጠብቀው ከ50 ሰዎች ሳይበልጡ መከናወን ይችላሉ
  • ከቤት ውጪ የአካል እንቅስቃሴና የማኅበረሰብ ስፖርት ርቀታቸውን ጠብቀው ከ100 ሰዎች ሳይበልጡ መከናወን ይችላሉ
  • የመዋኛ፣ የእንፋሎት ክፍሎችና ምንጮች ግልጋሎቶችን አንድ ሰው በአራት ስኩየር ሜትር ርቀት መጠቀም ይቻላል
ልዩ ሥነ ሥርዓቶች

  • ሠርግ በውጭና ቤት ውስጥ ሲካሄዱ ማኅበራዊ ርቀት እንደተጠበቀ ሆኖ ገደብ አይኖራቸውም፤ የዕድምተኞች ኤሌክትሮኒክ ሬኮርድ ሊያዝ ይገባል።  በግል መኖሪያዎች ሲካሄዱ ማኅበራዊ ርቀት እንደተጠበቀ ሆኖ ከ30 ዕድምተኞች ሊበልጡ አይገባም። 
  • ቀብር  በውጭና ቤት ውስጥ ሲካሄዱ ማኅበራዊ ርቀት እንደተጠበቀ ሆኖ ገደብ አይኖራቸውም። የለቀስተኞች ኤሌክትሮኒክ ሬኮርድ ሊያዝ ይገባል። በግል መኖሪያዎች ሲካሄዱ ማኅበራዊ ርቀት እንደተጠበቀ ሆኖ ከ30 ዕድምተኞች ሊበልጡ አይገባም
  • ቤተ እምነቶች በውጭና ቤት ውስጥ ሲካሄዱ ማኅበራዊ ርቀት እንደተጠበቀ የምዕመናን ኤሌክትሮኒክ ሬኮርድ ሊያዝ ይገባል (ሁኔታው ካልፈቀደ በወረቀት ላይ ማስፈር ግድ ይላል)
 


Share

Published

By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service