ከዲሴምበር 26-30/ታህሣሥ 16-20 የሚካሔደው 27ኛው የእግር ኳስ ቶርናመንት በሜልበርን-አውስትራሊያ ሁለተኛ ቀኑን አስቆጥሯል። በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የታደሙ የማኅበረሰብ አባላትና የዝግጅቱ አስተባባሪ የሆኑት የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር አመራር አባላት ስለ ዓመታዊ የእግር ኳስና ባሕላዊ መሰናዶዎች ሂደት ይናገራሉ። የማኅበሩ ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው በበኩላቸው ዓርብ ዲሴምበር 29 / ታህሣሥ 19 የሚከበረው የኢትዮጵያ ቀን "አንድነትን የምናከብርበትና ባንዲራችንን ከፍ አድርገን የምናውለበልብበት ቀን ነው" በማለት የማኅበረሰቡ አባላት በዕለቱ በሥፍራው እንዲገኙ ጥሪያቸውን ያቀርባሉ።
አንኳሮች
- የ27ኛው ዓመታዊ የስፖርት በዓል መክፈቻ
- የውድድር ውጤቶች
- ሽልማቶች
Share





