Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

"ከአዝማሪና" እስከ "ትዝታ ንግሥና"፤ ዝነኛው አንጋፋ ድምፃዊ ጌታቸው ካሣ ከእዚህ ዓለም በሞት ተለየ

Getachew Kassa.jpg
Singer Getachew Kassa. Credit: PR

ድምፃዊ ጌታቸው ካሣ ከ SBS አማርኛ ሬዲዮ ጋር በሕይወ ሳለ ባካሔደው ቃለ ምልልስ ስለ ሙዚቃ ሕይወት ጉዞው አውግቷል።


Published

By Stringer Report

Source: SBS



Share this with family and friends


ድምፃዊ ጌታቸው ካሣ ከ SBS አማርኛ ሬዲዮ ጋር በሕይወ ሳለ ባካሔደው ቃለ ምልልስ ስለ ሙዚቃ ሕይወት ጉዞው አውግቷል።


አንኳሮች

  • አዝማሪና የሙዚቃ ፍቅር
  • ከሸክላ አድማጭነት ወደ መድረክ ባለቤትነት
  • ከስደት ወደ አገር ቤት

አንጋፋው ድምፃዊ ጌታቸው ካሣ በ'የካቲት 12' ሆስፒታል ሕክምና ሲከታተል ቆይቶ ትናንት ለሊት ሕይወቱ አልፏል።

ድምፃዊ ጌታቸው በ1960ዎቹ እና 1970ዎቹ በኢትዮጵያ በበርካታ ትላልቅ የሙዚቃ ክለቦች በመስራት ታዋቂነትን ማትረፍ ችሎ ነበር።

ጌታቸው ከሙዚቃ ሥራዎቹ ውስጥ "ብርቱካን ነሽ ሎሚ፣ ሀገሬን አትንኳት፣ ውብ አዲስ አበባ፣ ሳይሽ እሳሳለሁ፣ የከረመ ፍቅር" እና በሌሎች በርካታ ዘፈኖቹ ከፍ ያለ አድናቆትና ዕውቅናን አግኝቶባቸዋል።

አንጋፋው ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ ሙዚቃን ከ 6 አመቱ ጀምሮ የተጫወተ ሲሆን በፈጣን ባንድ ፣ ሸበሌ ባንድ ፣ የቬነስ ባንድ እና በኋላም ከዋልያስ ባንድ ጋር በመሆን የተለያዩ ይዘት ያላቸውን የሙዚቃ ስራዎችን ተጫውቷል።

ጌታቸው “ትዝታ እና ፈጣን” በሚባል የሙዚቃ ስልቶች ተወዳጅ የነበረ ሲሆን ከተጫወታቸው ተወዳጅ ዜማዎች መሃከል "ሀገሬን አትንኳት "፣ አዲስ አበባ" ፣ “ትዝ ባለኝ ግዜ”፣ "የከረመ ፍቅር” ፣ “መሄዴ ነው" ፣ "ሳይሽ እሳሳለሁ" የተሰኙት የሚጠቀሱ ናቸው።


Latest podcast episodes

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now