የተሰውት ዝክረ መታሰቢያ በጦር ሜዳ ለወደቁቱ በአንዛክ ቀን የሚነገር ሥነ ግጥም ነው። SBS ከአውስትራሊያ የጦር መታሰቢያ ጋር በመተባበር አማርኛን አካትቶ በ45 ቋንቋዎች አቅርቧል።
በአንዛክ ቀን፤ አውስትራሊያውያን በመላ አገሪቱ በአውስትራሊያና ኒውዝላንድ ጦር ኃይሎች ለግዳጅ ተሠማርተው ያገለገሉ፣ የተዋጉና የተሰውን ይዘክራሉ።
በሂደትም የዝክረ መታሰቢያው ቀን ግዘፍ እየነሳ እንደመጣ በጦር ሜዳ በተቃራኒ ወገን ተሰልፈው የነበሩትንም አካትትቷል።
የተሰውት ዝክረ መታሰቢያ ሥነ ግጥምን በአማርኛ እነሆን፤
እነርሱን እርጅና አያገኛቸውም፤ እኛ ለእርጅና እንደተዳረግን ሁሉ።
ዕድሜ ለድካም አይዳርጋቸውም፤ ዓመታትም አይኮኑኗቸውም።
ፀሐይ ስትጠልቅና ጎህ ሲቀድ
እናስባቸዋለን።

ስለ አውስትራሊያ አንዛክ ቀን ተጨማሪ መረጃ ካሹ Australian War Memorial ድረ ገጽን ይጎብኙ።
Share






