በጉዲፈቻ ዙሪያ በየጊዜው የሚሰሙ አሉታዊ ታሪኮች ቢኖሩም ሃና እና ቤተለሄም ግን አውስትራሊያዊት በሆኑት የጉዲፈቻ እናታቸው አማካኝነትም ህይወታቸው ውጤታማ መሆኑን ይናገራሉ።

.

Source: Betty and Hanna

ሃና ስኪል እና ቤተለሄም ስኪል ይባላሉ :- ሃና በሶስት አመቷ ከጎጃም እንዲሁም ቤተልሄም በአራት አመቷ ከደሴ ከተሞች ነበር ወደ አውስትራሊያዊት የመጡት ። አውስትራሊያዊት በሆኑት የጉዲፈቻ እናታቸው አማካኝነትም እህትማማቾች ለመሆን ችለዋል። ምንም እንኳ በጉዲፈቻ ዙሪያ በየጊዜው የሚሰሙ አሉታዊ ታሪኮች ቢኖሩም ሃና እና ቤተለሄም ግን በጉዲፈቻ እናታቸው ሳቢያ ህይወታቸው ውጤታማ መሆኑን ይናገራሉ። “ ለወላጅ እናቴ ትልቅ ከበሬታ እና ሀዘኔታ አለኝ ። በእሷ አእምሮ ልጇን አሰልፎ መስጠት ምን ያህል ከባድ እንደሚሆን አውቃለሁ።እሷ አሳልፋ ስለሰጠችኝ ያገኘሁትን እድል ሳስበው እድለኛ አድርጋኛለች። ሃና ስኪል” “ የጉዲፈቻ እናታችን ፍቅሯ ሙሉ ለሙሉ ለእኔ ነበር።ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ነው ፍቅሯን የሰጠችኝ።በቂ የሆነ ፍቅር ለሁላችሁም አለኝ ነው የምትለን።እኔም ለእሷ ያለኝ ፍቅር እንደ እናትም አባትም ነው ። ቤተልሄም ስኪል "



Share

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now