“ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ለማመን የሚከብድ ሰው የሚባል ባህሪን የማይገልጽ ነው አዝነናል ልባችንም ተሰብሯል” - ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ

LR- Abune Petros and Melake Selam Mengistu Source: Supplied
ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ የሰሜን አሜሪካ እና ኒውዮርክ አካባቢ ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም መላክ ጸሃይ መንግስቱ ሀይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ የምስራቅ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ አህጉረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ እንዲሁም የብሪዝበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ፤ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ በሰጡት ቃለምልልስ በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አመታት በህዝቡ ላይ በቅርቡ ደግሞ በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ የታዩት ጥቃቶች ለማመን የሚከብድ ሰው የሚባል ባህሪን የማይገልጽ ፤ ልብን በሃዝን የሚሰነጥቅ ድርጊቶች ናቸው ብለዋል ፡፡ እንዲህ አይነት ክስተቶች በተለይ በውጭ በሚኖረው ማህበረሰብ ውስጥ ጭንቀት እና የእንቅልፍ እጦትን ፤በመፍጠር የእርስ በእርስ ግንኙነት ላይ የሚጥለው ጠባሳ እጅግ ከባድ ነው ሲሉ የሃይማኖት አባቶቹ ገልጸዋል ፡፡ በዚህ አጋጣሚም በተፈጠሩት ችግሮች ሳቢያ ከአእምሮ ጤና ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶችን የሚያስተናግዱ ሁሉ በአቅራቢያቸው ያሉ የእምነት ተቋማት እርዳታ ቢሹ መልካም እንደሆነ ምክራቸውን ለግሰዋል ፡፡
Share