አገር ቤትና ባሕር ማዶ - “ለትግሪኛ ሙዚቃ ዕድገት እጄ አለበት።” አንበሳ ግርማይ

My Story: Anbesa Girmay

አንበሳ ግርማይ Source: Courtesy of AG

አንበሳ ግርማይ - ድምጻዊ፣ የዘፈን ግጥም ገጣሚና ክራር ተጫዋች ነው። ኑሮው በአገረ አውስትራሊያ ሲሆን፤ የሕይወት ታሪኩ መነሻ የትውልድ ከተማው ከሆነችው አሥመራ ነው።


የውልደትና ዕድገት ሽርቦሽ ሆኖ፤ አንበሳ ለጋ ወጣት ሳለ ሙዚቃ - የሕይወት ጥሪው ሆነች።

ለመጀመሪያ ጊዜ መድረክ ላይ እንዲወጣ አጋጣሚውን የፈጠረለት የእናት አገር ጥሪ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ነው። ያኔ የቀበሌ ኪነት ቡድን አባል ነበር።

የአንበሳ የሙዚቃ ጉዞ በቀበሌ ኪነት አልተወሰነም። ወደ ከፍተኛ ከፍ አለ። 

Anbessa Girmay
Source: Courtesy of AG

ሲልም፤ ወደ ውትድርና ሕይወት አመራ። ይሁንና ውትድርናው ጠብመንጃ እንዲጨብጥ እንጂ ክራሩን ይዞ መድረክ ላይ እንዲገዝፍ ባለመፍቀዱ የውትድርና ሕይወትን እምቢኝ ብሎ ወደ ሲቪል ሕይወቱ አመራ። ይሁንና ያለ ሕጋዊ ስንብት ከውትድርና ዓለም መውጣት “በከጂነት” ያስጠይቃልና የአምስት ዓመት እስራት ተበይኖበት ዘብጥያ ወረደ።

ከእሥር እንደወጣ ያመራው ወደ ቀጣና የኪነት ቡድን ነበር። ብዙም ሳይቆይ ግና የኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባር ኤርትራን ሲቆጣጠር እንደሌሎች ኢትዮጵያውያን ሁሉ አሥመራን ለቅቆ ወጣ። አዲግራት - ትግራይ ገባ።

እንደ ኤርትራ ሁሉ ኢትዮጵያም በኢሕዲሪ መንግሥት ግርሰሳ ሳቢያ በኢሕአዲግ መዳፍ ውስጥ ነበረች። አፍላ የነበረው ጉዳይም የሽግግር መንግሥቱን ቻርተር የማጽደቅ ጉዳይ ነበር። እምብዛም ሳይቆይ አሥመራ ሳለ በሙዚቃ ሕይወቱ የሚያውቁት የአዲግራት ቀበሌ ኪነት አባላት እንዲቀላቀላቸው ግብዣ አቀረቡለት። አምበሳም ስለ ቻርተሩ አዲስ ግጥማና ዜማ ከውዝዋዜ ጋር አቀናብሮ እነሆኝ አላቸው።

Anbessa Girmay
Source: Courtesy of AG

አዲግራት ላይ ጠቅሎ መስፈር ስላልፈለገ ወደ አዲስ አበባ አቀና። ተክለ ሃይማኖት ሠፈር ካገኛቸው የኤርትራና የትግራይ የኪነ ጥበብ ወዳጆቹ ጋር ሆነው “ወልዋሎ” ባንድን አቆሙ። የሙዚቃ ሕይወታቸውንም መግፋት ጀመሩ።

Anbessa Girmay
Source: Courtesy of AG

አንበሳ ወደ አገረ አውስትራሊያ በ2007 ዓ.ም. መጥቶ እስከቀረ ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ የአማርኛ፣ ትግርኛና ትግረ ታዋቂ ድምጻውያንን በመድረክና በስቱዲዮ ካሴት ቀረጻ አጅቧል።

በአውስትራሊያ ሕይወቱም ከቤተሰቡ ድጋፍ ጋር ከሙዚቃ ሥራው አለተለየም።

Anbessa Girmay
Source: Courtesy ofAG

የሙዚቃ ሕይወቱን በምልሰት ተመልክቶ ለትግርኛ ሙዚቃ ያበረከታቸውን አስተዋጽዖዎቹን ሲገልጥ ያለው “ ለትግርኛ ሙዚቃ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጌያለሁ። የትግሪኛ ሙዚቃ አሁን ላለበት ዕድገት የእኔ እጅ አለበት። በዚያም እኮራለሁ” የሚል ነው።

  


Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
አገር ቤትና ባሕር ማዶ - “ለትግሪኛ ሙዚቃ ዕድገት እጄ አለበት።” አንበሳ ግርማይ | SBS Amharic