በሕይወት ዘመናቸው ስለ "እኛና አብዮቱ" መፅሓፋቸው ሲናገሩ "ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መሆኗ ይቆጨኛል፣ ያናድደኛል፣ ያሳዝነኛል። ወደብ አልባ ሀገር ነፃ ሀገር አይደለም። መጪዎቹ የኢትዮጵያ መንግሥታት የሚያስቡበት ጉዳይ ይመስለኛል" ያሉት የቀድሞው የኢትዮጵያ ሕዝባዊት ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ ዘርፈ ብዙ አተያዮች። (ምልሰታዊ ምልከታ
አንኳሮች
- እኛና አብዮቱ
- ከአየር ኃይል ወደ ደርግ አባልነት
- 'አጀንዳ አልባ' የቀ.ኃ.ሥ ከፍተኛ ባለ ስልጣናት ግድያ
- የሌ/ጄኔራል አማን አንዶም የዘመነ አብዮት ሚናና ፍፃሜ
- የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አሟሟት አለመገለጥ
- የመኢሶንና ኢሕአፓ ዘመነ አብዮት አዎንታዊና አሉታዊ ሚናዎች
- ከምሥራቅ ወደ ሰሜን ጦር ግንባር
- የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ድል የመነሳት አስባቦች
- የደርግ / ኢሕዲሪ ጠንካራ፣ ደካማና ጎኖችና ጥፋቶች
- የወደብ ጉዳይ
- ምስጋናና ማስገንዘቢያ
ጄኔራል አማን አንዶም 'ኤርትራ ትገንጠል' የሚለውን ግልፅ አቋም ብዙ ጊዜ አያንፀባርቁም። ፌዴሬሽን እንዲፈጠር ፍላጎት አላቸው። ጀብሃና ሻዕቢያን ለማስታረቅ ብዙ ሙከራ፣ ብዙ ጥረት አድርገዋል። በእኛ በኩል ግን ይህ ፍፁም የሚሆን ነገር ሆኖ አልተገኘም።የቀድሞው የኢትዮጵያ ሕዝባዊት ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ
ትልቅ የግንዛቤ እጥረት አለ። ነገሮችን ሰፋ አድርጎ መመልከት ይገባል። የኢትዮጵያ ሠራዊት የተሸነፈው በወያኔ ሠራዊት እንዳልሆነ መታወቅ ያለበት ይመስለኛል። የ17 ዓመት እንቅስቃሴ ውጤት ነው። እኛ የተዋጋነው በጣም ከብዙ ኃይሎች ጋር ነው። ለተቃዋሚዎች እርዳታ የሚያደርጉ የውጭ ኃይሎች ነበሩ።የቀድሞው የኢሕዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ
ወደፊትም የውጭ ኃይሎች (ምዕራባውያን፣ ዓረቦችና ጎረቤት ሀገሮች) ፍላጎታቸው እስካልተሟላላቸው ድረስ የኢትዮጵያን መንግሥት መቃወማቸው አይቀርም። አለያ ለእነሱ ፍላጎት ሀገሪቱን ክፍት ማድረግ አለብን። እኛ ደግሞ ነፃነትን እየጠበቅን፤ የኢትዮጵያን ክብር የምናስጠብቅ ሰዎች ነን ብለን ስለምናምን፤ ፍላጎታቸውን ልናሟላላቸው አልቻልንም። እናም ሊያጠፉን ተነሱ።የቀድሞው የኢሕዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ
እኔ እንዲያውም መሸነፋችን ሳይሆን የሚገርመኝ፤ ለ17 ዓመት መቆየታችን ነው። ከነበረብን ጠላትና ችግር አንፃር።የቀድሞው የኢሕዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ
እኛ ደሃ ሆነን እንደገባን፤ ደሃ ሆነን ነው የወጣነው።የቀድሞው የኢሕዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ
ለኢትዮጵያ ሕዝብ አክብሮትና ምስጋና አለኝ። መልካም አንደሠራን ሁሉ ጥፋቶችንም ሠርተናል። ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማሳሰብ የምፈልገው፤ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያዊነት መቆየት የምትችለው፣ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን ብለን በኩራት ልንኖር የምንችለው፣ ልጆቻችንና የልጅ ልጆቻችንም ኢትዮጵያውያን ነን ብለው መኖር የሚችሉት፤ አንድነታችን ሲጠበቅ ብቻ ነው።የቀድሞው የኢሕዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ
Share






