Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

ወደ ጎን የተገፋውታሪክ፤ የአቦርጂናልና ቶረስ ሰርጥ ደሴተኞች አገልግሎት በአንዛክ ቀን

First Nations Anzac

The Australian War Memorial For Our Country memorial recognises the military service of Aboriginal and Torres Strait Islander peoples. Credit: Tracey Nearmy/Getty Images

በየዓመቱ አውስትራሊያውያን የአውስትራሊያና ኒውዝላንድ ጦር ሠራዊት ኮር ቀን (አንዛክ ቀን) ለማክበር ይታደማሉ። እኒያን በጦርነቶች፣ ግጭቶች እና የሰላም አስከባሪ ግዳጆች ተሰማርተው አገልግሎቶቻቸውን አበርክተው የነበሩትን በክብር ለመዘከር። ይሁንና የምንዘክረው የእነ ማንን ታሪክ ነው? አዘውትረን የማንሰማቸው ታሪኮችስ አሉ? በእዚህ ክፍለ ዝግጅት በጣም ጠቃሚ የሆነ ግና ቸል የተባለ ታሪክን እናነሳለን፤ የአቦርጂናልና ቶረስ ሰርጥ ደሴት ሰዎችን አገልግሎት።


Published

Updated

By Rachael Knowles, Roza Germian

Presented by Lowanna Grant

Source: SBS




Share this with family and friends


በየዓመቱ አውስትራሊያውያን የአውስትራሊያና ኒውዝላንድ ጦር ሠራዊት ኮር ቀን (አንዛክ ቀን) ለማክበር ይታደማሉ። እኒያን በጦርነቶች፣ ግጭቶች እና የሰላም አስከባሪ ግዳጆች ተሰማርተው አገልግሎቶቻቸውን አበርክተው የነበሩትን በክብር ለመዘከር። ይሁንና የምንዘክረው የእነ ማንን ታሪክ ነው? አዘውትረን የማንሰማቸው ታሪኮችስ አሉ? በእዚህ ክፍለ ዝግጅት በጣም ጠቃሚ የሆነ ግና ቸል የተባለ ታሪክን እናነሳለን፤ የአቦርጂናልና ቶረስ ሰርጥ ደሴት ሰዎችን አገልግሎት።


Key Points

  • የአውስትራሊያ ጦር መዘክር 1200 የአቦርጂናል ወንዶች በአንደኛው የዓለም ጦርነት እንዲሁም 6,500 በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ለውትድርና ለመመልመል ሞክረው እንደነበር ግምቱን አሳድሯል
  • ነባር ዜጎች በጦር ሠራዊት ውስጥ ለመመልመል በርካታ መሰናክሎች ገጥሟቸዋል
  • በርካቶች ለምልመላ ለመብቃት ዝርያቸውን እስከ መደበቅ ደርሰዋል
  • ከዘመቻ መልስም መድልዖና የሕግ ገደቦች ለነባር ዜጎች የጦር አባላት የዕለት ተዕለት ሕይወት ነበር

    በርካታ አቦርጂናልና ቶረስ ሰርጥ ደሴት ሰዎች ምንም እንኳ በይፋ ከቀጠራ ቢታገዱም በአንደኛና ሁለተኛ የዓለም ጦርነቶች ወቅት ነባር ዜጎች ካልሆኑ የአውስትራሊያ ጦር ሠራዊት አባላት ጎን ለጎን ተሰልፈው አገልግለዋል።  

    ዛሬ፤ ታሪካቸው ዕውቅና እንዲያገኝና ለዝክረ መታሰቢያም እንዲበቃ የሚደረጉ ጥረቶች ጠንክረዋል።

    የንጉናዋል/ጎሜሮይ ሰው ማይክል ቤል የእዚያ ሥራ አካል ናቸው። እንደ የአውስትራሊያ ጦር መታሰቢያ አገናኝ መኮንንነታቸው እኒያ የአቦርጂናልና ቶረስ ሰርጥ ደሴተኞች ሰዎች የጦር ደንብ ለብሰውና በሌላም በኩል በሀር ቤት ለጦርነቱ ጥረቶች የየድርሻ አገልግሎትና መስዋዕትነታቸው ያበረከቱቱ ተነቅሰው፤ ሲልም ዕውቅና እንዲቸራቸው እገዛ አበርክተዋል።

    በእዚህ ሥራም፤ ግልፅ ምስል ብቅ ብሎ መታየት ጀምሯል።  

    ምን ያህል የአቦርጂናልና ቶረስ ሰርጥ ደሴተኛ ሰዎች በአንደኛው የዓለም ጦርነትና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት አገልግለዋል?

    “በአሁኑ ወቅት ከ1200 ትንሽ ከፍ ያለ የነባር ዜጎች ወንዶች በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ተቀጥረዋል ወይም ለመመልመል ሙከራ አድርገዋል፤ እንዲሁም 6,500 ያህል ወንዶች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ለቅጥር በቅተዋል” ሲሊ አቶ ቤል ገልጠዋል።

    Indigenous Australians Honoured On Anzac Day At Coloured Diggers March
    Understanding ANZAC Day means recognising the contributions and challenges faced by Aboriginal and Torres Strait Islander peoples.  Credit: Brendon Thorne/Getty Images

    ቁጥሮቹም የተጨማሪ ሬኮርዶች መገኘትን ተከትለው እየጨመሩ ነው።  

    ምንም እንኳ እንከን ቢበዛባቸውም፤ ቁጥሮቹ ቀላል የሚባሉ አይደሉም።

    The rates of enlistments or attestations are the same as their non-Indigenous brothers and sisters.
    Michael Bell

    የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች በውትድርና ለመቀጠር ገጥመዋቸው የነበሩ ጋሬጣዎች ምን ነበሩ?

    ነባር ዜጎቹ በጦር ሠራዊት ውስጥ ለመቀጠር ገጥመዋቸው የነበሩ ገደቦች ዘርፈ ብዙ ነበሩ።

    በአገር ውስጥ ከዳር እስከ ዳር የመንቀሳቀስ ገደቦች ነበሩባቸው።  

    እንደ ሙሉ የአውስትራሊያ ዜጎችም አይቆጠሩም ነበር። ሌላው ቀረቶ እንደ ሰው እንኳ ሕጋዊ ዕውቅና አልነበራቸውም።

    ወታደራዊ ፖሊሲዎችም አውሮፓዊ ዝርያ ያላቸውን ካልሆነ በስተቀር ሌሎችን አካታች አልነበሩም።  

    እኒህም አንድ ላይ ተጣምረው ሁነኛ መሰናክሎችን ፈጥረውባቸዋል።

    እንዲያም ሆኖ ግና፤ በርካታዎቹ ለቀጠራ በአዋኪ ሁኔታዎች ውስጥ አልፈዋል። እኩል መብቶችን ለነፈገቻቸው ሀገር ለማገልገል ብርቱ ፍላጎት፣ ፅንዓትና ቁርጠኝነትን አሳይተዋል።

    Aboriginal And Torres Straight Islander Veterans
    A wreath is laid during the annual ANZAC coloured diggers service in Sydney. Credit: Lisa Maree Williams/Getty Images

    ነባር ዜጎቹ ከጦር ሜዳ ሲመለሱ የጠበቋቸው ምንድን ነበሩ?

    ለበርካታ የነባር ዜጎች ወታደሮች መስዋዕትነት እኩልነት ማለት አልነበረም።

    ወደ ሕብረተሰቡ የተቀላቀሉት፤ መድልኦና የገደብ ሕጎች የዕለት ተዕለት ሕይወት አካል ሆነው ሳለ ነው። 

    አቶ ቤል “ወንዶቻችን ለመብቶች በውጭ ጦርነት ተፋልመዋል፤ በገዛ አገራቸው ግና የመብቶች ባለቤቶች አልነበሩም” ሲሉ አመላክተዋል።

    አክለውም “ወደ ሀገራቸው የተመለሱት በእጅጉ እኩል ወደ አልነበረ ሕብረተሰብ ነበር። የተቀላቀሉትም ልየታ፣ የተጓደለ ሕጋዊ ዕውቅና፣ የመሬት ባለቤትነት፣ እኩል ክፍያ፣ ልጆቻችንን በማሳደግ ላይ ገደቦች በተጣሉበት፣ የትውልዶች ስርቆት በአያሌው ዕውን በሆኑበት ሁኔታ ነበር" ብለዋል።

    የተወሰኑ ነባር ዜጎች ጥቅማ ጥቅሞችን ማግኘት ቢችሉም፤ አያሌዎች ግና በመጠነ ሰፊ ማኅበራዊና ፖለቲላዊ ገደቦች ሳቢያ ድጋፍ አልባ በመሆን ተጠቃሚ አልነበሩም።

    ሌላው ቀርቶ ከሌሎች አብረዋቸው ካገለገሉ የቀድሞ ጦር አባላት ጋር እንኳ ለመገናኘት ያዳግታቸው ነበር።  

    የቀድሞና የወቅቱን ወታደሮች ለመዘከር የአንዛክ ቀን ክብረ በዓልን የሚያዘጋጀውና አልክሆልን ጨምሮ የመዝናኛ አገልግሎት ሰጪ የሆነው ከጦር ሜዳ ተመላሽ ወታደሮች ሊግ ክለብ ውስጥ የነባር ዜጎች የቀድሞ ወታደሮች ላይ ገደቦች ነበሩት። 

    አውስትራሊያ የአቦርጂናልና ቶረስ ሰርጥ ደሴተኞችን ወታደራዊ አገልግሎት አሁን የምንዘክረው እንደምን ነው?

    በቅርብ አሠርት ዓመታት ውስጥ የአውስትራሊያ ጦር መታሰቢያ የአቦርጂናልና ቶረስ ሰርጥ ደሴተኞችን አገልግሎት በመግለጥ ንቁ ሚና ከውኗል።  

    “በመላ ማዕከለ ስዕላታችን ታሪኮቻችን በእኩልነትና አግባብነት ተዳርሰዋል” ያሉት አቶ ቤል ሲሆኑ “የነባር ዜጎችን ጠቅላላ አገልግሎት፣ ሁሉንም ማዕከለ ስዕላት፣ ሁሉንም ውክልናዎቻችንን ያቀፉ ይዘቶች አሉን” ሲሉም አክለዋል።

    አያይዘውም “በወታደራዊ ደንብ ልብስ ራሳቸውን የሚያዩት እንደ ምድብ ክፍሎቻቸው አረንጓዴ፣ ሰማያዊ ወይም ግርጫ አድርገው ነው፣ በጦር ሠራዊቱ፣ አየር ኃይልና ባሕር ኃይል የደንብ ልብሶች” ብለዋል።

    በርካታ ነባር ዜጎች ራሳቸውን የሚያዩት በቅድሚያ ከሌሎች ጎን ተሰልፎ እንዳገለገለ ወታደር ስለ መሆኑ አንፀባራቂ ነው።   

    Aboriginal And Torres Straight Islander Veterans
    The annual ANZAC coloured diggers event in Sydney celebrates the contributions of Aboriginal and Torres Strait Islander servicemen and servicewomen. Credit: Lisa Maree Williams/Getty Images

    በእዚህ አንዛክ ቀን ስለ አቦርጂናልና ቶረስ ሰርጥ ደሴተኞች ታሪክ ማወቅ የሚገባዎት ምንን ነው?

    አንዛክ ቀንን መረዳት ማለት የአቦርጂናልና ቶረስ ደሴተኞች ስለ አበረከቷቸው አስተዋፅዖዎችና ለገጠሟቸው ተግዳሮቶች ዕውቅናን መቸር ነው።

    “ዛሬ ላይ ደርሶ ስላለው ሙሉዕ የአውስትራሊያ ታሪክ ነው” ሲሉ ያመላከቱት አቶ ቤል “ባለፉት ዓመታት ለዕይታ ያልበቃን እንደነበርን ማለት አይደለም። እንደ አንደኛው የዓለም ጦርነት ማንነታቸውን እንደደበቁትም አይደለም፣ የአውስትራሊያን ሙሉዕ ታሪክ እንዲያዩ ነው የምናበረታታው። ዕውቅናን ነፍገው ተፅፈው እንደነበሩት ያለፉት ሥርቶች ሳይሆን” ብለዋል።

    የአንዛክ ቀን እኒህን በጦርነቶችና ግጭቶች ውስጥ አገልግሎቶቻቸውን የሰጡትን መዘከሪያ፤ ለታሪክ ክብር ለመቸርም በጋራ መታደሚያ ነው።  

    ስለ አዲሱ የአውስትራሊያ ሕይወትዎ ተጨማሪ ጠቃሚ መረጃና ፍንጮች ለማግኘት የአውስትራሊያ ስትገለጥ ፖድካስትን ይከተሉ አሊያም ደንበኛ ይሁኑ።   

    ጥያቄዎች ወይም ርዕሰ ሃሳቦች ካለዎት? 

    australiaexplained@sbs.com.au ኢሜይል ይላኩልን።


    Latest podcast episodes

    Follow SBS Amharic

    Download our apps

    Watch on SBS

    SBS World News

    Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

    Watch now