Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

በአውስትራሊያ የእርዳታ እና በግል የሚሰበሰብ ገንዘብ አካሄድ ምን ይመስላል?

BlurGettyImages-1075808762.jpg

募款人员必须清楚说明慈善机构的性质和职责。 图片来源:Scott Barbour / Cricket Australia via Getty Images

የእርዳታ ገንዘብን ስናሰባስብ ልንከተላቸው የሚገቡ ህጎች ምንድን ናቸው ? ላለመጭበርበራችን ምን ማርጋገጫ አለን ? እርዳታን መለገስ የሚፈልጉ ከሆነ ፤ ወይም አሰባሳቢ አልያም በኦንላይን በጋራ የእርዳታ ማሰባሰብን የሚያደርጉ ከሆነ ማወቅ የሚገባዎት ህጎች የሚከተሉት ናቸው ።


Published

Updated

By Zoe Thomaidou

Presented by Martha Tsegaw

Source: SBS



Share this with family and friends


የእርዳታ ገንዘብን ስናሰባስብ ልንከተላቸው የሚገቡ ህጎች ምንድን ናቸው ? ላለመጭበርበራችን ምን ማርጋገጫ አለን ? እርዳታን መለገስ የሚፈልጉ ከሆነ ፤ ወይም አሰባሳቢ አልያም በኦንላይን በጋራ የእርዳታ ማሰባሰብን የሚያደርጉ ከሆነ ማወቅ የሚገባዎት ህጎች የሚከተሉት ናቸው ።


አንኳሮች

  • የገንዘብ ማሰባሰብ እንዴት እንደሚካሄድ የሚመለከቱ ህጎች በአውስትራሊያ ውስጥ ከአንድ ግዛት እና ሌላኛው ይለያያል ።
  • የገንዘብ ማሰባሰቢያ ማጭበርበርን ለማስወገድ፣ የበጎ አድራጎት ተቋሙ ህጋዊ መሆኑን ለማረጋገጥ ጊዜ ይውሰዱ፣ ጥርጣሬ ካለም ልገሳውን አያድርጉ።
  • የገንዘብ ማሰባሰብ ህጎችና የፈቃድ (licence) መስፈርቶች ለአነስተኛ ማሰባሰቢያዎች እና ለኦንላይን ጥሪዎችም ይተገበራሉ፤ ስለዚህ በእርስዎ ሁኔታ የሚመለከተውን መመርመር ይኖርብዎታል።
  • የእርዳታ ተቋሙ ሕጋዊ መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እችላለሁ?
  • ለእርዳታ የምለግሰው ገንዘብ በታክስ ሰአት ላይ ሊቀነስ ይችላል?
  • ገንዘብ ማሰባሰብን ማን ይቆጣጠራል?
  • እርዳታ አሰባሳቢው አጭበርባሪ መሆኑን እንዴት ማወቅ ይቻላል?
  • ለአንድ የተለይ ዓላማ ገንዘብ እያሰባሰብኩ ከሆነ ምን ማወቅ አለብኝ?
  • በኦንላይን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ጥሪዎች ህጎች ምንድን ናቸው?

በአውስትራሊያ ያሉ የበጎ አድራጎት ተቋማት፣ ከአካባቢያዊ የማኅበረሰብ ቡድኖች ጀምሮ እስከ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ድረስ በተለያየ መጠንና አወቃቀር ይገኛሉ።

ሁሉም አነስተኛ የበጎ አድራጎት ተቋማት፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ተቆጣጣሪ በሆነው የአውስትራሊያ የበጎ አድራጎትና ከትርፍ ውጭ ድርጅቶች ኮሚሽን (ACNC) ዘንድ መመዝገብ አይጠበቅባቸውም።

የእርዳታ ተቋሙ ሕጋዊ መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እችላለሁ?

አንድ የበጎ አድራጎት ተቋም ACNC Charity register. ዘንድ በይፋ የተመዘገበ መሆኑን ማረጋገጥ በጣም ቀላል ነው።

በAustralian Charities and Not-for-profits Commission (ACNC) መመዝገብ ማለት አንድ ተቋም የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች እንዳሟላ እና ከትርፍ ውጭ እንደሚሰራ በይፋ የተረጋገጠ ነው ማለት ነው። እንዲሁም በመንግሥት የተቀመጡ ደንቦችን ማክበሩን ያሳያል ይላሉ ሱ ዉድዋርድ (Sue Woodward)

ማንኛውንም እርዳታ ከመስጠት በፊት ተቋሙ በACNC ዘንድ መመዝገቡን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። ይህም ገንዘቡ የሚተዳደርበትን ፣ ገንዘቡ የሚውልበትን እና ምንጩን ለማወቅ ያግዛል።

“በትክክል የተመዘገበ የበጎ አድራጎት ተቋም መሆኑን ማወቅ ለጋሾች ልብ ሙሉ እንዲሆኑ ያግዛል፤ እንዲሁም እነዚህ ድርጅቶች በመንግሥት ሕጎች መሠረት የመልካም አስተዳደር መስፈርቶችን እንዲከተሉ ይገደዳሉ። "

ለእርዳታ የምለግሰው ገንዘብ በታክስ ሰአት ላይ ሊቀነስ ይችላል?

በአውስትራሊያ፣ ለበጎ አድራጎት የሚሰጥ ልገሳ በታክስ ላይ ቅናሽ (tax deduction) ሊያገኝ ይችላል። ነገር ግን የታክስ ቅናሽ ለማግኘት የተቋሙ በAustralian Taxation Office (ATO) ዘንድ Deductible Gift Recipient status. የተረጋገጠ መሆን አለበት።

ይህን ለማረጋገጥ የተቋሙን መረጃ በ ABN Lookup ማየት ይቻላል ።

“የታክስ ቅናሽ ለመጠየቅ ካሰቡ የልገሳዎን ማረጋገጫ (መቀበያ ደረሰኝ) እንደ መዝገብ ያስቀምጡ።”

Australia Explained - Fundraising
Not all registered charities can issue tax deductible receipts for donations. Credit: FujiCraft/Getty Images

ገንዘብ ማሰባሰብን ማን ይቆጣጠራል?

በአውስትራሊያ ውስጥ እያንዳንዱ ግዛትና ክልል የራሱ የገንዘብ ማሰባሰብ ሕጎችና ተቆጣጣሪ ባለስልጣናት አሉት።

Australian Charities and Not-for-profits Commission (ACNC) የገንዘብ ማሰባሰብ ተቆጣጣሪ አይደለም ሲሉም ኮሚሽነር ዉድዋርድ ይገልጻሉ።

“ለምሳሌ፣ አንድ ድርጅት በገበያ ማዕከል ከሕዝብ ገንዘብ እየሰበሰበ ከሆነ፣ በእያንዳንዱ ግዛት የሚለያዩ ልዩ ደንቦችን መከተል ይኖርበታል።”

በተጨማሪም የገንዘብ ማሰባሰቢያዎች የአካባቢ መንግሥት ፈቃዶችን እና ሌሎች ህጎችን ማክበር ይኖርባቸዋል፤ ለምሳሌ Australian Consumer Law እና Privacy laws.

አንድ የበጎ አድራጎት ድርጅት የገንዘብ ማሰባሰብ አካሄዱ ላይ ጥርጣሬ ካለዎት ወደ የክልሉ ወይም የግዛቱ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ማመልከት ይችላሉ።

የገንዘብ ማሰባሰብ ህጎችን እና የአካባቢ ተቆጣጣሪዎችን ለማወቅ ለበለጠ መረጃ ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ ።

የተመዘገበ የበጎ አድራጎት ተቋም ገንዘቡን በተሳሳተ ወይም በህገወጥ መንገድ እየተጠቀመ ነው ብለው ካመኑ፣ report it to the ACNC.  ይችላሉ።”

“ይህንንም በምስጢር ፣ ማንነትዎን ሳይገልጹ ማድረግ ይቻላል፤ እኛም የሰዎችን ጥርጣሬ በትኩረት በመውሰድ እንመረምራለን” ሲሉ ኮሚሽነር ዉድዋርድ ተናግረዋል።

Australia Explained - Fundraising
Be on the lookout for fake appeals, especially following a disaster or tragic event. Credit: bymuratdeniz/Getty Images

እርዳታ አሰባሳቢው አጭበርባሪ መሆኑን እንዴት ማወቅ ይቻላል?

በድረገጽ የሚደረግ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ማጭበርበርን ለመለየት፣ ድረገጹ ህጋዊ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

ጥርጣሬ ካለዎት፣ እና የሚሰበስበውን ሰው በአካል ቢያውቁትም እንኳን፣ ገንዘብ በፍጹም አትለግሱ ሲሉ Peter Hills-Jones ይመክራሉ።

እርሱ የPublic Fundraising Regulatory Association ዋና ስራ አስኪያጅ (CEO) ሲሆኑ፣ ይህ ድርጅት በአውስትራሊያ በፊት ለፊት የሚደረግ የበጎ አድራጎት እና የገንዘብ ማሰባሰብ ዘርፍ ውስጥ ያሉ ድርጅቶችን የሚወክል ኤጀንሲ አካል ነው።

" አባባል፡ ጊዜ ይውሰዱ፣ ትንሽ ይጠብቁ፤ ሁልጊዜ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ ወይም የእርዳታ ተቋሙ ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ስልክ በመደወል ያረጋግጡ። ከዚያ በኋላ ልግስናዎን ያድርጉ።
Peter Hills-Jones

አቶ ሂልስ ጆንስ በአካል ፊት ለፊት የሚደረግ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ማጭበርበር እንደተደርገበት ሊያመለክቱ የሚችሉ ሶስት ዋና የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን ይገልጻሉ፦

  • ግለሰቡ የደንብ ልብስ (uniform) አልለበሰም
  • ፎቶ ያለበት መታወቂያ አይያዝም
  • ገንዘብ በጥሬ ገንዘብ (cash) ወይም አንድ ጊዜ ብቻ የሚከፈል ልገሳ እንዲሰጥ ይጠይቃሉ

Fundraising at football
Face-to-face fundraisers are mandated to behave with professionalism and respect. Credit: James Wiltshire/AFL Photos via Getty Images

በአካል ፊት ለፊት የሚደረጉ የገንዘብ አሰባሳቢ ሰራተኞች ፤ ከበሬታና ሙያዊ ስነ-ምግባር ሊኖራቸው ይገባል፤ ለምሳሌ ሰዎችን ከሚያደርጉት ነገር ማደናቀፍ ወይም ተቀምጠው ያሉበት ቦታ ሄዶ ማነጋገር አይፈቀድላቸውም።

ገንዘብ ሰብሳቢዎቹ የበጎ አድራጎት ተቋሙ ምን እንደሚሰራ እና ገንዘብን ለምን እንደሚጠይቁ በግልጽ ሁኔታ መግለጽ አለባቸው።

በጎዳና ላይ ወይም ቤት ለቤት በሚደረግ የገንዘብ ማሰባሰብ ወቅትም፣ ሰዎች ገንዘብ መስጠት ካልፈለጉ ውሳኔያቸው መከበር አለበት። አንድ ሰው የገንዘብ ማሰባሰቢያው ማጭበርበር ነው ብሎ ከተጠራጠረ፣ ገንዘቡን መስጠት የለበትም ፤ እንዲሁም ወዲያውኑ ለአካባቢው ተቆጣጣሪ ወይም ለብሔራዊ national Scamwatch service.ማሳወቅ አለበት ።

ለአንድ የተለይ ዓላማ ገንዘብ እያሰባሰብኩ ከሆነ ምን ማወቅ አለብኝ?

ገንዘብ የሚያሰባስቡ ግለሰቦች፣ የገንዘብ አሰባሰቡ ሂደት ከሕግ አንጻር ያለውን አካሄድ ፤ እንዲሁም ከአንድ ግዛት ወይም ክልል እንደሚለያይ ማስታወስ ይኖርባቸዋል።

ኤሚ ዊሊያምስ ከ Justice Connect Not-for-profit Law አገልግሎት ጠበቃ እንደሚመክሩት ያሉትን ህጎችን በተመለከተ ፤ የገንዘብ ማሰባሰብን የሚቆጣጠረውን ተቋም ህጎች ማረጋገጥ እንዳለባቸው ይመክራሉ።

“ለምሳሌ፣ ወደ ውጭ አገር ለበጎ ፈቃድ ጉዞ ለመሄድ ከጓደኞች ወይም ከቤተሰብ ገንዘብ መጠየቅ ወይም በስራ ቦታ ለአንድ ሰራተኛ የሕክምና ወጪ ለመክፈል ገንዘብ ማሰባሰብ እንደ ተለምዶ በገንዘብ ማሰባሰብ ህጎች አይቆጠሩም” ሲሉ ወ/ሮ ዊሊያምስ ያብራራሉ።

Australia Explained - Fundraising
There are three main types of face-to-face fundraisers: street, door-to-door and fundraisers operating within shopping centres. Credit: LeoPatrizi/Getty Images

በኦንላይን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ጥሪዎች ህጎች ምንድን ናቸው?

አንድ የገንዘብ ማሰባሰቢያ በኦንላይን ለማስጀመር፣ ለምሳሌ በcrowdfunding platform መድረክ የሚጠቀሙ ከሆን ፤ በብዙ ክልሎች የሚሰሩ የገንዘብ ማሰባሰብ ህጎችን ማክበር የማይቀር ነው ይላሉ ሚስ ዊሊያምስ ።

“በኦንላይን ላይ በክራውድፈንዲንግ (crowdfunding) ገንዘብ እያሰባሰቡ ከሆነ፣ በእያንዳንዱ ግዛትና ክልል ፈቃድ (licence) ሊያስፈልግዎ ይችላል።
Amy Williams

“አንዳንድ የክራውድፈንዲንግ (crowdfunding) መድረኮች መመሪያ ይሰጣሉ፤ ነገር ግን አንዳንዶቹ መመሪያቸው በጣም ግልጽ አይሆንም፣ ስለዚህ የራስዎን የህግ ምክር መፈለግ ይኖርብዎታል።”

በመጨረሻም፣ እሳቸው እንደሚሉት ፤ በኦንላይን ላይ ገንዘብ የሚያሰባስቡ ሰዎች የሚሰበሰበውን ገንዘብ ለምን እንደሚያውሉት በግልጽ ሁኔታ መግለጽ አለባቸው፣ ይህም ለጋሾች ግራ እንዳይገባቸው ያደርጋል።

“ለጋሾችም እንዲሁ ‘የዚህ ድርጅት ዓላማ ምንድን ነው?’ ብለው መጠየቅ አለባቸው፤ ይህም ገንዘቡ ለምን ተግባር እንደሚውል ግልጽ ይሆንላቸዋል ።”

Subscribe to or follow the Australia Explained podcast for more valuable information and tips about settling into your new life in Australia.

Do you have any questions or topic ideas? Email australiaexplained@sbs.com.au


Latest podcast episodes

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now