ሰዓሊ ወርቅነህ በዙ "ስኬታማ ነኝ ብዬ አስባለሁ" ይላል። በኢትዮጵያ የሥነ ስዕል ዓለም ውስጥ የበኩሉን ምን ዓይነት የሥነ ጥበብ አስተዋፅዖዎችን እንዳበረከተና ሰሞኑን ዩኔስኮ ኒው ዮርክ ላይ ባሰናዳው ሲምፖዚየም ስላቀረባቸው የጥበብ ሥራዎቹና ስለተበረከተለት ሽልማት ይገልጣል።
ስኬት
ሰዓሊ ወርቅነህ በዙ፤ በሥነ ጥበቡ ሕይወት ስኬታማ መሆኑን ይገልጣል።
ያም ሊሆን የቻለው "በትክክል የሚያስተምሩ መምህራኖችን ማግኘቴና በትክክል ጥበበን መግለፅ መቻሌ የመጀመሪያው ሲሆን፤ ሁለተኛው ላለፉት 20 ዓመታት የሙሉ ጊዜ አርቲስት ሆኔ መሥራት መቻሌ ነው" ሲል ያስረዳል።
ይህም "ጥበቡን አንድ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ አድርሽያለሁ ማለት ነው" ሲልም የጥበብ በረከት አስተዋፅዖ እሳቤውን አመላክቷል።

ወርቅነህ ብዙዎቹ በአገር ውስጥና በባሕር ማዶ የተወደዱለት ሥራዎቹ ከአማልክት ጋር የተያያዙ ናቸው።

ሰዓሊ ወርቅነህ የሥነ ስዕል ሥራዎቹን በማሊ፣ ግብፅ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ስዊትዘርላንድና ፊንላንድ አቅርቧል።
ሰሞኑንም በኒው ዮርክ በተዘጋጀ ሲምፖዚየም የጥበብ ሥራዎችን አቅርቧል።
ሽልማትም አግኝቶበታል።

ውጥኖች
ከቅርብ ጊዜ የወርቅነህ ውጥኖች አንዱ የስዕል ሥራዎቹን ፖርቱጋል ውስጥ ላለ አንድ ስቱዲዮ ለማቅረብ ስምምነት ላይ መድረሱ ነው።
የረጅም ጊዜ ትልሞቹ አንድ የግል ጋለሪ ማቋቋምና ታዳጊ የጥበብ ሰዎች ሕዝብና አገር ከቸሩት ትሩፋት ማጋራት ነው።







