የኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስን ግንኙነት ለማሻሻል ሲልም ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ምን መደረግ አለበት?

US Flag (L) and Ethiopians wave their national flag (R). Source: Getty
ዶ/ር ዮናስ ብሩ - የቀድሞው የዓለም ባንክ ሉላዊ ምጣኔ ሃብት ንፅፅር ምክትል ሥራ አስኪያጅ “ብዙ በአሜሪካ፣ አፍሪካና የተባበሩት መንግሥታት ትላልቅ ባለስልጣናትን የሚያውቁ ኢትዮጵያውያን ስላሉ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነሱን አሰባስበው አፍሪካውያን ከእኛ ጋር እንዲቆሙ፤ አሜሪካውያንም እንዲያደምጡ ብዙ ግፊት መደረግ አለበት” ሲሉ፤ ዶ/ር አክሎግ ቢራራ - የቀድሞው የዓለም ባንክ ገዲብ የምጣኔ ሃብት አማካሪ በበኩላቸው “ ‘ኢትዮጵያ የአሜሪካ ወዳጅ እንጂ ጠላት አይደለችም’ በማለት ሳንሰለች ማስረዳት አለብን። የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ፖሊሲ የመርህ ምሰሶዎቹ እኔን ጨምሮ ለብዙዎች ግልፅ አይደለም። ዳያስፖራው መንግሥትን ሊተካ ስለማይችል፤ መንግሥት አመራሩን መያዝ አለበት” ይላሉ።
Share