Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

“ በአረብ አገር ሴት የማርሻል አርት እና ቴኳንዶ አስልጣኝ ሆኜ ለመስራት ተጨማሪ ጥረትን እና ችሎታን ማስመስከር ግድ ብሎኝ ነበር ። ” -አትዮጵያ ጌታቸው

Ethiopia Getache
E,Getachew.

ኢትዮጵያ ጌታቸው የቀድሞ የኳታር በሄራው ቡድን የማርሻል አርት እና ቴኳንዶ አሰልጣኝ ወደዚህ ሙያ ለመግባት ያሳለፈቸውን ውጣ ውረድ እና የደረሰችበትን ስኬት አጫውታናለች።


Published

Updated

Presented by Martha Tsegaw

Source: SBS



Share this with family and friends


ኢትዮጵያ ጌታቸው የቀድሞ የኳታር በሄራው ቡድን የማርሻል አርት እና ቴኳንዶ አሰልጣኝ ወደዚህ ሙያ ለመግባት ያሳለፈቸውን ውጣ ውረድ እና የደረሰችበትን ስኬት አጫውታናለች።


አንኳሮች

  • ማርሻል አርት እና ሴቶች
  • ማርሻል አርት አካልን እና ጭንቅላትን የሚያንጽ አርት ነው
  • ከኳታር የተገኙ ትርፋቶች

ኢትዮጵያ ጌታቸው የቀድሞ የኳታር በሄራው ቡድን የማርሻል አርት እና ቴኳንዶ አሰልጣኝ ስትሆን ወደዚህ ሙያ የተቀላቀለችው ገና የዘጠኝ አመት ታዳጊ በሆነችበት እድሜዋ ነበር ።

አሰልጣኝ ኢትዮጵያ ከሰልጣ
E Getachew

አጀማመሯም የተስተካከለ የአካል ብቃት ማሰልጠኛ በሌለበት በመውደቅ፤ በመነሳት ፤ በመሰበር እና በማገገም አሰልቺ እና አስቸጋሪ በሆነ የስልጠና ጊዜ ነበር ትላለች።

አሰልጣኝ ኢትዮጵ ከኳታር ቴኳንዶ ብሄራዊ  ቡድን አባላት ጋር
E, Getachew.

ዛሬ ሙያ አድርጋ የያዘችውን የማርሻል አርት እና ቴኳንዶ ከመሰረቱ ጀምሮ አሰልጥኖ ለዚህ ያበቃትም ሁሌም ከአፏ የማትለየው ማስተሯ እና ወንድሟ አየናቸው ጌታቸው ነበር ።

ኢትዮጵያ የባህር ማዶ ህይወቷን በዱባይ ብትጀምርም ሙያዋን በተግባር እንድታውል በሯን ከፍታ የተቀበለቻት አገር ግን ኳታር ነበርች። እንደ ኢትዮጵያ አባባልም የኳታር መንግስት ለስፓርት ከሚሰጠው ከፍተኛ ትኩረት እና እገዛ የተነሳ እሷም የአገሪቱን የብሄራዊ ቡድን በማርሻል አርት እና ቴኳንዶ ለማሰልጠን እድሉ አግኝታ ቡድኑን ከውጤት ጋር ለ11 አመታት ያህል አሰልጥናለች።

2DE3803C-6B63-4230-A21B-EC6C3E301387.jpeg
E, Getachew

ኢትዮጵያ በአሁን ሰአትም ባለችበት ኳታር በግል አሰልጣኝ በመሆን እያገለገለች ትገኛለች።


Latest podcast episodes

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now