አቶ ነዓምን ዘለቀ - የቀድሞው የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አባልና የውጭ ጉዳይ ኃላፊና ዶ/ር ዮሃንስ ገዳሙ በGeorgia Gwinnette College የፖለቲካ ሳይንስ መምህር መጪውን የኢትዮጵያ አገር አቀፍ ምርጫ አስመልክተው ይናገራሉ። ዶ/ር ዮሃንስ “ይህ ምርጫ ፋይዳው ትልቅ ነው። ምክንያቱም ኢትዮጵያ በሕዝብ የተመረጠ፤ ሕዝባዊ ተቀባይነት ያለው መንግሥት ይኖራታል ማለት ነው” ሲሉ፤ አቶ ነዓምን በበኩላቸው “በአብላጫ ወይም በጥምር መንግሥትነት የሚመጣው መንግሥት ሕጋዊነትና ቅቡልነት እንዲኖረው ምርጫው በጣም አሥፈላጊ ነው” ይላሉ።
Share






