የፊፋ የዓለም ዋንጫ ዓለምን በአንድ ላይ እያሰባሰበ ነው ስንል ማጋነን አይደለም። ለዚህም ምክንያቱ እግር ኳስ በዓለም ላይ በጣም ታዋቂው ስፖርት ተብሎ ስለሚታወቅ ነው። ይሁን እና የእግር ኳስ መነሻው በአካባቢያችን ባሉ የስፖርት ሜዳዎች (suburban ovals) እና በአካባቢ ክለቦች ውስጥ ነው፤ ጨዋታው እድሜ እና ችሎታቸው የተለያየ የሆኑ ተጫዋቾችንም ያሳትፋል። እርስዎም ከእነዚህ ተጫዋቾች አንዱ መሆን የሚችሉበትን መንገድ እነሆ።
Key Points
- እግር ኳስ ሰዎች ከየትም ቢመጡ፣ ምንም ዓይነት ጾታ፣ ዕድሜ ወይም ችሎታ ቢኖራቸው ሁሉንም አንድ ላይ ያሰባስባል።”
- “የእግር ኳስ (Walking football) እና ፉትሳል (Futsal) በአውስትራሊያ በፍጥነት እያደጉ ካሉ ሁለት የእግር ኳስ ዓይነቶች መካከል ይገኛሉ።”
- “በPlay Football ድረ-ገጽ ላይ የአካባቢዎን የእግር ኳስ ክለብ ማግኘት ይችላሉ። Play Football የFootball Australia የማህበረሰብ እግር ኳስ ዲጂታል መድረክ ነው።”
- ይህንን ጨዋታ ምን ብለን እንጥራው?
- እግር ኳስ ለምን በጣም ታዋቂ ሆነ?
- እንዴት መጀመር እችላለሁ?
- እግር ኳስ በእርግጥ ለሁሉም ሰው የሚሆን ነው?
- ዓመቱን ሙሉ መጫወት እችላለሁ?
- የተለያዩ የእግር ኳስ ዓይነቶች አሉ?
- ስለ እግር ኳስ በጣም ከፍተኛ ፍላጎት ካለኝ ምን ማድረግ እችላለሁ?
ይህንን ጨዋታ ምን ብለን እንጥራው?
በመጀመሪያ በጣም አስፈላጊውን ጥያቄ እንመልስ፡ ይህንን ጨዋታ ‘ፉትቦል’ ወይም ‘ሶከር’ ብለን እንጠራው?”
“የFootball Australia የእግር ኳስ ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር የሆኑትን ሄዘር ጋሪዮክን ጠይቀናቸዋል።”
“እኔ እንደማስበው በአውስትራሊያ ይህንን ጨዋታ ‘ፉትቦል’ ብለን መጥራት አለብን። ይህ የዓለም አቀፍ ጨዋታ ነው።”
ብለዋል ።
እግር ኳስ ለምን በጣም ታዋቂ ሆነ?
እግር ኳስ እጅግ አካታች የሆነ ስፖርት ሲሆን፣ በመላው አውስትራሊያ 1.9 ሚሊዮን ተሳታፊዎች አሉት።
ይህ በአገሪቱ በብዛት ሰዎች የሚሳተፉበት ስፖርት ሲሆን በፍጥነትም እያደገ ነው” ሲሉ ሚስ ጋሪዮክ ይናገራሉ። “በአውስትራሊያ ከ87 በላይ ዜግነት ያለቸው እና ከ35 በላይ የተለያዩ የቋንቋዎችን የሚናገሩ የእግር ኳስ ተጫዋቾችን ያቀፉ ቡድኖች አሉ። እግር ኳስ በአገሪቱ በጣም አካታች ስፖርት መሆኑንም በጣም እንኮራበታለን።”
የእግር ኳስ ታዋቂነት የሚመጣው የሰዎችን የትውልድ አመጣጥ፣ ጾታ፣ ዕድሜ ወይም ችሎታ ሳይለይ በቀላሉ አንድ ላይ ማሰባሰብ መቻሉ ነው።”
እድሜያቸው አራት ወይም ከአምስት ዓመት በላይ የሆኑ ሁሉ በአካባቢያቸው የእግር ኳስን መጫወት ይችላሉ፤ ወይም የአካል ብቃታቸው እምብዛም የሆኑት የWalking Football ቡድንን መቀላቀል ይችላሉ።”

እንዴት መጀመር እችላለሁ?
Football Australia የሚያስፈልጉዎትን ሁሉም መረጃዎች ይዟል።
Play Football platform, የFootball Australia ይፋዊ የማህበረሰብ እግር ኳስ ዲጂታል ገጽ ነው።”
“ ይህ በመላው አገሪቱ ያሉ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች፣ ዳኞች እና በፈቃደኝነት የሚሰሩ ሰዎች የሚጠቀሙበት መድረክ ነው። እንዲሁም ምዝገባዎ በሁሉም ክለቦች፣ ውድድሮች እና አባል ፌዴሬሽኖች ዘንድ እውቅና እንዲኖረው ያደርጋል” ሲሉ ሚስ ጋሪዮክ ያብራራሉ። ”
ይህ በአካባቢዎ ካለው ክለብ ለመመዝገብ የሚችሉበት ነው።
“ በመላው አውስትራሊያ ከ2000 በላይ ክለቦች አሉ፤ እያንዳንዱም ክለብ ወደ እግር ኳሳችን የሚገቡ እጩዎች የሚገኙበት ነው” ሲሉ የFootball NSW የማህበረሰብ እና የአባላት አገልግሎት ኃላፊ አሮን ዲብዲን ይናገራሉ።
ከተለያዩ አገሮች ባህሎች መጥተው በአውስትራሊያ የሚኖሩ በርካታ የእግር ኳስ ተጫዋቾች አሉ ። ክለቦቻችንም ሁሉም ሰው መጥቶ እንዲሳተፍ መልካም አቀባበል የሚያደርጉና የጓደኝነተን ስሜት የሚፈጥሩ ናቸው ። ”

እግር ኳስ በእርግጥ ለሁሉም ሰው የሚሆን ነው?
የዚህ ጨዋታ መሠረታዊ መርህ አካታች የሚል ነው። ለወጣቶችና ለአዛውንቶች፣ ለቀደምት የአውስትራሊያ ነዋሪዎች (First Nations ) ተጫዋቾች፣ ልዩ ፍላጎትና የተለያዩ ችሎታዎች ላላቸው ተጫዋቾች፣ እንዲሁም ከተለያዩ ባህል እና ቋንቋዊ ለመጡ የማህበረሰቦች ክፍሎችን የሚያካትት ነው። ”
“የFootball Australia ድረ ገጽን ሲመለከቱMiniRoos Settlement Program and the Multicultural Youth Programፕሮግራሞችን ያገኛሉ።”
እነዚህ ከFootball Australia ጋር በመተባበር የሚካሄዱ ነፃ ፕሮግራሞች ናቸው” ሲሉ አቶ ዲብዲን ያብራራሉ።
“እነዚህ ሁለቱም ፕሮግራሞች ሰዎች ወደ እግር ኳሱ በቀላሉ እንዲገቡ የመጀመሪያ መንደርደሪያ እንዲሆኑ ታስበው የተዘጋጁ ናቸው። ተጫዋቾች የመጀመሪያ የእግር ኳስ ስልጠና ፕሮግራም እንዲያደርጉ፣ በጨዋታው እንዲሳተፉ፣ እንዲሁም ከክለቦች ጋር እንዲገናኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል ። በመጨረሻም ከ600 በላይ ከሆኑት ክለቦቻችን አንዱን በመቀላቀል አባል እንደሚሆኑ ተስፋ እናደርጋለን፤ ምክንያቱም ክለቦቻችን የማህበረሰባችን ናቸውና ።”
“እንደነዚህ ያሉ ፕሮግራሞች ሰዎች በማህበረሰባቸው እና በእግር ኳሱ ማህበረሰብ ያለውን ክፍተት እንዲጠብ የሚረዱ አይነተኛ መንገዶች ናቸው።”አረን ዲብዲን
የማህበረሰባዊ አንድነት ገጽታው ነበር ላል ሮቻን ታክሉምን ወደ ማህበረሰብ እግር ኳስ የሳባት።
በኩዊንስላንድ በሚገኘው SSI Multicultural Sports Club በኩል በተዘጋጀ ነፃ የሴቶች የእግር ኳስ ፕሮግራም መሳተፍ ጀመረች፤ ከዚያም በኋላ አልተለየችም።”
“ ከዚያም በMSC ውስጥ በመሳተፌ ወደ መደበኛ የእግር ኳስ ክለብም መቀላቀል ቻልኩ። ብዙ ጊዜ ለሌሎች ወጣቶች የምነግረው ፤ ስፖርት ሰዎችን አይለይም ወይም አያገልም ይርሚለውን ነው ፤ ይህም ተቀባይነት እንዳለዎተንዲሰማዎት ያደርጋል ። ”
ዓመቱን ሙሉ መጫወት እችላለሁ?
እግር ኳስን እንደ ክረምት ጨዋታ ታውቁት ይሆናል፤ ነገር ግን በNSW ብቻ ወደ 80,000 የሚጠጉ ተጫዋቾች ለበጋ እግር ኳስ ይመዘገባሉ።”.
የበጋ ወይም ከውድድር ወቅት ውጭ የሚካሄደው እግር ፤ ኳስ ራሱን የቻለ ትልቅ ስፖርት ነው። በክረምት ወቅት የማይጫወቱ ነገር ግን ጨዋታውን ለመሞከር ለሚፈልጉ ሰዎችን ጥሩ አማራጭ ነው ” ሲሉ አቶ ዲብዲን ይናገራሉ።
“ብዙ ሰዎች የበጋ እግር ኳስን ሲሞክሩ እንደሚወዱት እናያለን፤ ከዚያም በቀጣዩ ዓመት ለክረምት የክለብ እግር ኳስ ይመዘገባሉ።”
በአነስተኛ ቡድኖች እና በትንሽ ሜዳ ላይ የሚጫወቱም ስለሆነ፣ ለመሳተፍ ቀላል እና ዘና የሚያደርግ ጨዋታ ነው።
“ ሰዎች በክረምት የሚጫወቱት ጨዋታ ላይ የማይሞክሯቸውን አንዳንድ ብልሃቶች ወይም አስደሳች ነገሮች በዚህ ጨዋታ ላይ ለመሞከር ይችላሉ። ጫናው ዝቅተኛ የሆነ ግን ደግሞ የበለጠ አዝናኝ ነው። ”Aaron Dibdin

የተለያዩ የእግር ኳስ ዓይነቶች አሉ?
ሰዎች በዓለም ላይ በፍጥነት እያደጉ ካሉ የቤት ውስጥ መካከል አንዱን መሞከር ይፈልጉ ይሆናል። ፉትሳል ከእግር ኳስ በተለየ በትንሽ ሜዳ ላይ የሚጫወት የእግር ኳስ ዓይነት ነው። ፈጣን፣ ኃይለኛ እና ብቃትን የሚጠይቅ ጨዋታ ተብሎም ይገለጻል፤ ብዙ ምርጥ ተጫዋቾችም ዛሬ ያሉበት ደረጃ እንዲደርሱ አስተዋጽኦ አድርጓል።
በሰውነት ላይ ዝቅተኛ ጫና የሚያሳድር ስፖርት ይፈልጉም ይሆናል።
Ms Garriock says walking football is also experiencing major growth.
ሚስ ጋሪዮክ የWalking Football (በመራመድ የሚጫወት እግር ኳስ) እንዲሁ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ መሆኑን ይናገራሉ።
ከሁሉም በላይ የሚያስደስተው በሚሳተፉበት እና አባል በሚሆኑበት ቡድን የተጫዋቾች ህብረት አካልመሆንዎ ነው።
አህመድ ጋይሳሪ ኒያ በሜልበርን ከአካባቢው ካውንስል በኩል ባገኘው Walking Footballን የተቀላቀሉ ሲሆኑ ፤ ይህ ጨዋታ ልባቸው እንዲመታ እና ሰውነታቸው እንዲንቀሳቀስ እንደረዳቸው ይናገራሉ ።
Walking Football ቀላል ጨዋታ ብቻ ነው ብለው እንዳያስቡ፤ ላብን ጠብ የሚያደርግ እንዲሁም ጥሩ ስሜትን የሚፈጥር ጨዋታ ነው ።አህመድ ጋይሳሪ ኒያ
ነገር ግን እግር ኳስን ለ50 ዓመታት እንደትጫወቱት እንደ አቶ ጋይሳሪ ኒያ በተመሳሳይ ኃይል መጫወት አያስፈልግዎትም። Walking Football በሰውነት ላይ ዝቅተኛ ጫና እንዲኖረው እና ማህበራዊ ግንኙነትን እንዲያሳድግ በሚል መርህ የተዘጋጀ ነው።
መጋጨት (tackling) ወይም መሮጥ አይፈቀድም። በሰውነት ላይ ዝቅተኛ ጫና ስለሚያሳድርም፣ የጤና ችግኝ ላላቸው ወይም በራስ መተማመናቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ሰዎችም ተስማሚ የሆነ ስፖርት ነው። በተጨናሪም ለሁሉም ዕድሜ የሚሆኑ የWalking Football ስልጠናዎችን ማግኘት ይችላሉ።
“ መጀመሪያ ስሄድ ለመሞከር ብቻ ነው ብዬ ነበር ። ነገር ግን መጀመሪያ ጊዜ ከተሳተፍኩ በኋላ በጣም ድንቅ እንደሆነ ተረዳሁ” ሲሉ አቶ ጋይሳሪ ኒያ ይናገራሉ። Walking Football “ከዚህ በፊት እንደዚህ ያለ ተሞክሮ ላልነበራቸው እና እንደ እኔ ላሉ ዕድሜ ላላቸው ሰዎች በጣም የሚያስደስት ነው። በእርግጥ እኔ 73 ዓመቴ ነው።”

ስለ እግር ኳስ በጣም ከፍተኛ ፍላጎት ካለኝ ምን ማድረግ እችላለሁ?
ሄዘር ጋሪዮክ እያንዳንዱ ሰው ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለመድረስ የራሱ የሆነ መንገድ እንዳለው ትናገራለች።
“ ጥሩ ተጫዋች ከሆኑ እና የከፍተኛ ደረጃ ልማት መንገድን መከተል ከፈለጉ፣ መጀመሪያ ከክለብዎ መጀመር ያስፈልጋል። ከዚያም ከክለብዎ በመቀጠል የአካዳሚ አካል የሆነ የወጣቶች A-League ክለብ ማግኘት ይችላሉ። ከዚያም በመቀጠል የEmerging Championships ይገኛል፤ ይህም የሚያድጉ የMatildas እና Socceroos ተጫዋቾችን የሚያሳድግ ፕሮግራም ነው። በዚህ ውስጥም 14፣ 15 እና 16 ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ተጫዋቾች የሚያካትቱ የአገር በቀል (Indigenous) ቡድኖቻችን አሉ። እንዲሁም የወጣቶች ብሔራዊ ቡድኖቻችን ከ16 ዓመት በታች ደረጃ ይጀምራሉ። ”
በአውስትራሊያ ሕይወትዎን በተሻለ ሁኔታ ለመጀመር የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎችንና ምክሮችን ለማግኘት፣ Australia Explained ፖድካስትን (Subscribe) ያድርጉ ውይም ድረ- ገጻችንን ይከተሉ (Follow)።
ጥያቄ ወይም ሊብራራ የሚገባ ሀሳብ አለዎት? ወደ australiaexplained@sbs.com.au ኢሜይል ይላኩ።






