SBS Examines: ኢሚግሬሽን የቤት ቀውስን ያባብሳል?

Aerial of suburban Melbourne and CBD

The impact of migrants on the housing crisis is small, despite what some suggest. Source: Getty / Charlie Rogers

አውስትራሊያ የቤት እጥረት ቀውስ ተጋርጦባት አለ። በሌላም በኩል የባሕር ማዶ ፍልሰተኞች ቁጥር ሬኮርድ መመዝገብ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከቶውንም ከፍተኛውን ደረጃ ይዞ ይገኛል። የፍልሰተኞች ቁጥር መናር የቤት ግዢ / ግንባታና የኪራይ ዋጋዎች እንዲያሻቅቡ ያደርጋል?


የፍልሰተኞች ቁጥር ለቤት ዋጋ ማሻቅብ አስባብ መስሎ ይታያል፤ ሆኖም የመስኩ ተጠባቢዎች በዋዛ እንዲያ መፈረጁ ቀላል እንዳልሆነ ይናገራሉ።

በአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ ጡረተኛ የሥነ ሕዝብ ፕሮፌሰር ፒተር ማክዶናልድ፤ አተያዩ ትኩረት ሳቢ ሊሆን እንደሚችል ለ SBS ሲያመላክቱ፤

"ፖለቲከኞችና አተያየት ሰንዛሪዎች የቤት ገበያ ማሻቀብን ከኢሚግሬሽን ጋር አያይዘው ሲገልጡ፤ የፖሊሲ መፍትሔ የሚሻውን የቤት ቀውስ ትኩረትን ወደ ሌላ አቅጣጫ እያመላከቱ ነው"

"ይህ ቀውስ ነው፤ እናም በይፋ ሊነገር ይገባል። ይሁንና ሳቢያው ኢሚግሬሽን ስለሆነ፤ 'ኢሚግሬሽን ሲቀነስ፤ ችግሩ ይከላል' በማለት የሚከላ አይሆንም" ብለዋል።


Share

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now