የውይይት መድረክ “ የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን ማርች 8” - ክፍል አንድ

.

LR: Embet and Bertukan Source: SBS Amharic

የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን ማርች 8 በየአመቱ በአለም ዙሪያ የሚከበር ሲሆን አላማውም የተለየ ስልጣን እና ቦታ የሌላቸው ሴቶች ለመብቶቻቸው መከበር የከፈሉትን መሰዋትነት ፤ ያሳለፉትን ትግል እና ያስመዘገቡትን ውጤት ለመዘከር ነው። ሴቶች በትግላቸውም አንጻራዊ የሆኑ መብቶቻቸውን ለማስከበር ፤ ሰርተው ለመግባት የእድል በሮች የተከፈቱላቸው ቢሆንም በተቃራኒውም ሴቶች ዛሬም ድረስ በየትኛውም የአለማችን ክፍል ቢኖሩ የጾታ እኩልነታቸው አልተረጋገጠም። ዘንደሮም የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 ሲከበር በመርህ ደረጃ የሚያጎላው የጾታ እኩልነትን ነው። የዛሬውን የውይይት መድረክ ፕሮግራማችንን ማርች 8 የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ለመዘከር ይሆን ዘንድ ብለናል። የውይይታችን ተሳታፌዎች :- ወ/ሮ ብርቱካን ሽታዬ ቢያድግልኝ በቢሮ ኦፍ ሚቲሪዮሎጂ ክላይሜት ስፓሻል ዳታ የቡድን መሪ እንዲሁም በጂ ፒ ኤስ ሚቲሪዮሎጂ ተመራማሪ እንዲሁም ወ/ሮ እመቤት ታደሰ በናሽናል አውስትራሊያ ባንክ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ከፍተኛ አማካሪ ናቸው። በመላው አለም ለሚገኙ ሴቶች እና ለሴቶች እኩልነት ተቆርቋሪ ወንዶች ሁሉ “ መልካም የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን ማርች 8 ” ይሁን ::



Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service