ምርጫ 2022፤ የአውስትራሊያ ሌበር ፓርቲ

Source: Getty
የአውስትራሊያ ሌበር ፓርቲ እ.አ.አ በ1901 የተመሠረተ አንጋፋ ግራ ዘመም ተራማጅ ፓርቲ ነው። በአሁኑ ወቅት 68 የሕዝብ ምክር ቤት ወንበሮችን ይዞ በተቃዋሚ ፓርቲነት ቆሟል። ራሱን ችሎ መንግሥት ለመመሥረት በቅዳሜው ኤፕሪል / ግንቦት 13 ተጨማሪ 8 ወንበሮችን ማሸነፍ ይጠበቅበታል። ከአይሪሽ እናትና ጣሊያናዊ አባት የተወለዱት የፓርቲው መሪ አንቶኒ አልባኒዚ በለስ ቀንቷቸው ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ከበቁ፤ በአውስትራሊያ ታሪክ የመጀመሪያው ዝንቅ ዝርያ ያላቸው መሪ ይሆናሉ።
Share