ጌታእንዳለ ዘለቀ ነገራ፤ የልብ ሕመም ምርምር ሳይንቲስት ናቸው። በስኳር ሕመም አስባብ የሚከሰትን የልብ ድካም አስመልክተው ያቀረቡት የጥናታዊ ምርምር ግኝታቸው ከአሜሪካ የልብ ማኅበር የ Paul Dudley White International Scholar Award ተሸላሚነት አብቅቷቸዋል። ለሽልማት የበቁበትን የግኝት ውጤታቸውን ነቅሰው ያስረዳሉ። የስኳር ሕመምና የልብ ድካም ተያያዥነትን አስመልክተውም ማኅበረሰባዊ ምክረ ሃሳባቸውን ያጋራሉ።
አንኳሮች
- የስኳር ሕመምና የልብ ድካም ተያያዥነት
- የልብ ድካም ምልክቶች
- የምርምር ውጤት ስኬቶች
- አማራጭ የሕክምና መፍትሔዎች
- የሽልማት ፋይዳዎች
- ምክረ ሃሳቦች
Share






