ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንትና ተዋናይ ጌታሁን ይርጉ፤ ቅዳሜ ፌብሪዋሪ 28 / የካቲት 21 በሜልበርን ከተማ - አውስትራሊያ 21 Yardley St, Maidstone ከ4:00 pm - 6:00 pm ስለሚከበረው 130ኛው የአድዋ ክብረ በዓል መሰናዶና ዝግጅቶች ይናገራሉ። ማኅበረሰባዊ ጥሪም ያቀርባሉ።
አንኳሮች
- የአድዋ ትሩፋቶች
- ይቅርታ
- ምስጋና
- ሥነ ግጥም
- ኢትዮጵያዊ አንድነት
- ማኅበረሰባዊ ትብብር
አድዋ የፀዳ ኢትዮጵያዊነት ነው። ሰው ሆነን የምንገኝበት ቦታ አድዋ ነው። የራሳችንን አድዋ መሥራት አለብን፤ አንድ ላይ መቆም አለብን። ኮተታችንን ጥለን፤ ከጎሬያችን እንውጣ።ተዋናይ ጌታሁን ይርጉ
Share






