ምርጫ 2022፡ የአውስትራሊያ ሊብራል ፓርቲ

Australian Prime Minister Scott Morrison speaks to the audience at the Liberal Party election campaign launch on May 15, 2022 in Brisbane, Australia. Source: Getty
የአውስትራሊያ ሊብራል ፓርቲ - እ.አ.አ የቀድሞውን የተባበሩት አውስትራሊያን ፓርቲ በስያሜ ተክቶ የተመሠረተ ቀኝ ዘመም ወግ አጥባቂ ፓርቲ ነው። ከአውስትራሊያ ዋነኛ ፓርቲዎች አንዱ ሲሆን፤ ከአውስትራሊያ ናሽናልስ ፓርቲ ጋር ተቀናጅቶ በጥምር ፓርቲነት አውስትራሊያን በማስተዳደር ላይ ይገኛል። የፊታችን ቅዳሜ ሜይ 21 / ግንቦት 13 በሚካሔደው አገር አቀፍ ምርጫ በለስ ቀንቶት ዳግም ከተመረጠ አገረ አውስትራሊያን በማስተዳደሩ ይቀጥላል፤ ድል ከተነንሳም የተቃዋሚ ቡድን ሥፍራን ይዞ የፖለቲካ ብሔራዊ ጉዞውን ይቀጥላል።
Share