Settlement Guide: Australia’s First Peoples

Gooreng Gooreng Elder Uncle Richard Johnson Credit: Credit: Amy Chien-Yu Wang
የአውስትራሊያ ቀዳማይ ሰዎች ሥልጣኔ በቅርቡ በተካሄደ አንድ ዓለም አቀፍ የተመራማሪዎች ቡድን ጥናት መሠረት 50,000 ዓመታትን ያስቆጠረ የዓለማችን ጥንታዊ ሕይወት ያለው ሥልጣኔ ነው። ይሁንና፤ ስለ ነባር ሕዝቦቹ ታሪክ አውስትራሊያውያን የሚያውቁት ጥቂት ነው። በ2014ቱ የአውስትራሊያ ዕርቅ መልኪያ ሠንጠረዥ የሚያሳየው 30 ፐርሰንት ያህል አውስትራሊያውያን ብቻ ናቸው ስለ አቦርጂናልና ቶረስ ስትራይት ደሴት ባሕልና ታሪኮች ግንዛቤ አለን ያሉት። የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ዝርያቸው የሚመዘዘው ከአቦርጂናልና ቶረስ ስትራይት ደሴት ነው፤ በ2011ዱ የሕዝብ ቆጠራ መሠረትም ብዛታቸው በድምሩ ከጠቅላላው የአገሪቱ ሕዝብ ሶስት ፐርሰንት ነው። የ1788ቱ የአውሮፓውያን ሠፈራ በምድሪቱ ጥንታዊ ባለቤቶች ላይ ተከታታይነት ያላቸው አግላይ ፖሊሲዎች የሰብዓዊ መብቶቻቸውን በብርቱ ጎድተዋል፤ የልማዶች፣ ባሕልና ቋንቋዎች ዘለቄታን አውከዋል። Feature by Amy Chien-Yu Wang
Share