ሶሊያና እርሴ፤ ትንፋሽ አስዋጭ፣ የልብ ትርታን ደላቂ፣ ከዮጋም፣ ከጂምናስቲክም ልዩ አካላዊ እጥፋትና ዝርጋታን፣ ልዩ ምትሃት መሰል ክህሎትን ግድ የሚለው፤ ግና ሞገስን ተላብሶ መድረክ ላይ ግዘፍ የሚነሳ Contortionist Extraordinaire ኢትዮጵያዊት ናት። ድንቅ ክህሎቷም ከኤፕሪል 7 እስከ ሜይ 24 በሜልበርን ከተማ Meat Market ከClub Kabarett ጋር ለሕዝብ ዕይታ ይቀርባል። የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትም ታዳሚዎቿ እንዲሆኑ ትጋብዛለች።
አንኳሮች
- ከጎንደር እስከ አውስትራሊያ
- ከትግራይ ሰርከስ እስከ ዓለም አቀፍ መድረክ
- ማኅበረሰባዊ ግብዣ
Share






