የሰላ ብዕራቸውና ግና አብሯቸው አልተጠወረም። ከቶውንም በእፎእይታ ዘመናቸው እንዳይቦዝኑ ከደራሲነት ጎራ አሰልፏቸው አለ።

በዘውዳዊው ሥርዓት ዘመን የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አገር በቀል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሥልጣን እርከን ላይ ደርሰዋል።
በየካቲት ፷፮ቱ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮት ወቅት የጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥቱ መርማሪ ኮሚሽን ምክትል ሰብሳቢ ነበሩ።
በኋላም ኤርትራ ሉዓላዊ አገር እንድትሆን ተጋዳላይ ሆነው ታግለዋል። ሲልም፤ የኤርትራ ሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነዋል።
በረከት ሃብተስላሴ፤ ከአዲ ንፋስ የትውልድ ቀዬአቸው ተንስተው ለፊደል ቆጠራ እንደምን ወደ አሥመራ እንደአቀኑ፣ በባቡር ገስግሰው ሐረር እንደደረሱ፣ በጢያራ ከንፈው ከአዲስ አበባ ጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት ተማሪነት የሎንዶን ዩኒቨርሲቲ የሕግ ምሩቅነት እንደበቁ በምልሰት ያነሳሉ።
አገር ቤት ተመልሰውም ከዋና ተቆጣጣሪነት፣ ወደ ምክትል ዓቃቤ ሕግነት፣ አልፈውም ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ስለመድረሳቸውም ያወጋሉ።
የክፍል አንድ ውይይታችንን መንደርደሪያ ያደረግነው ‘ለምን ከልጅነት ጊዜዎ አንነሳም?’ በማለት ነው።





