አንኳሮች
- የኢትዮጵያ ሙዚቃ ዕድገትና ሂደት
- የፖፕና ሶል ድምፃዊት ኢሚሊያ ምትኩ
- የሀገር ቤት ትዝታዎች
የሀገራችን ሙዚቃ አድጓል ብሎ ለማለት ከባድ ነው። ሙዚቃ ለማደግ ብዙ ድጋፍን ይጠይቃል። የሀገሪቱ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ የፖለቲካ መዋቅርና ፖሊሲ፣ ፀጥታ፣ ሰላምና ፍቅሩ ሙዚቃው ላይ ተፅዕኖ ስለሚያሳድሩ። እነሱ ሳይስተካከሉ ሙዚቃ ብቻውን ሊያድግ አይችልም።ድምፃዊ ተሾመ ምትኩ
ሀገራችን ለኢትዮጵያ አይደለም ለዓለም ብቁ የሆነ ሙዚቃ ለማፍራት የሚያስችል ሰዎችን አፍርታለች። እነሱን አሰባስቦ፣ አመራር ሰጥቶ፣ ጥሩ መሪ ሆኖ መምራት ብቻ ነው የሚያስፈልገው ነው የምለው።ድምፃዊ ተሾመ ምትኩ
በሥነ ጽሑፍም፣ በሙዚቃም፣ በሌላም ያለ አርቲስት ከሕዝብ ከተለየ በኋላ ግማሽ ሰው ነው። ግማሽ ሰውነቱ ከሕዝብ ጋር ይቀራል። በሀገር ባለመኖር ቃላትም ጭምር ያጥራል። ፅንሰ ሃሳብም ይቀንሳል። ሰውነት ይረበሻል። ውጪ መኖር በራሱ ባለው የሙዚቃ ወይም ቲአትር አምድ ላይ aggressive ያደርጋል።ድምፃዊ ተሾመ ምትኩ
የሞራል ውድቀት አለ። አርባ - ሃምሳ ዓመት የተጫወቱ፣ ጥልቅ ዕውቀት ያላቸው ሙዚቀኞች፤ ውጪ ሀገር ፈረንጅ እንደ ብርቅ የሚያያቸውን ሀገር ቤት ውስጥ ግና ፍላጎቱ የለም። ውስጥ ያሉት ውጪ ያሉት ሙዚቀኞች እንዳይገቡባቸው ነው የሚፈልጉት። መንግሥትም ኢትዮጵያን በሚያፋቅር፣ በሚያስማማ፣ አንድ በሚያደርገን መልኩ ምንም ዓይነት ጥረት አያደርግም።ድምፃዊ ተሾመ ምትኩ
ልጄ ኢሚሊያን [ታዋቂ ኢትዮጵያዊት - ስዊድናዊት የፖፕና ሶል ድምፃዊት] ሁሌም 'ዕውቀት ያስፈልጋል። ዕውቀት ካለሽ ባንክ እንዳስቀመጥሺው ገንዘብ ቁጠሪው' እላት ነበር። ሀገር ወዳድ ናት። ኢትዮጵያን ትወዳለች። ጥሩ ኢትዮጵያዊት አርቲስት ናት።ድምፃዊ ተሾመ ምትኩ
ተጨማሪ ያድምጡ

አንጋፋው ድምፃዊ ተሾመ ምትኩ፤ ከሀገር ቤት እስከ አሜሪካ












