በደች ተክለአብ፤ ከሶማሊያ የ፲፩ ዓመታት እሥራት ቆይታ በኋላ እ.ኤ.አ. በ1988 ወደ ትውልድ አገራቸው ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
ግና እምብዛም ሳይቆዩ ወደ አገረ አሜሪካ አቅንተዋል። ዛሬም ድረስ ነዋሪነታቸው እዚያው ነው።
ከአፍሪካ ርቀው ቢኖሩም፤ አፍሪካ ከልባቸው አልወጣችም። ውስጣቸው ሰርጻ አለች።
የማንነት ስበቱ ግድ ብሏቸውም ከሚያስተምሩበት ዩኑቨርሲቲ ጋር ፕሮጄክት ነድፈው በቅርቡ ወደ ኡጋንዳ ዘልቀው ነበር።
የስደተኞችን ሕይወት በአይናቸው ተመልክተው፣ በኅሊናቸው ቀርጸው፤ በቀለም ቅባቸው ሕይወት አላብሰው ለዓለም የትድግና ጥሪያቸውን አቅርበውበታል። አሁንም ድረስ ‘የድረሱ፤ እንድረስላቸው' ጥሪያቸው አልተቋረጠም።
ስለ ማለፊያዎቹ የሕይወት ዘመን የቀለም ቅብ፣ ቅርፃ ቅርፅና የንድፍ ሥራዎቻቸንም አክለው አውግተውናል።


በክፍል ፫ ዝግጅታችን ስለ ቀደምት የአዲስ አበባ ሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት መምህራንን ሞገስ አላብሰው ያነሳሉ፤ ከሥነ ግጥም ገበታቸውም ያቋድሳሉ።

Kebedech Tekleab Source: Courtesy of KTA

Kebedech Tekleab Source: Courtesy of KTA

Behind Bars Source: Courtesy of KTA

River in Rwanda Source: Courtesy of KTA

The Power Source: Courtesy of KTA

Ash Source: Courtesy of KTA