የአድዋ ድል በተለይ በውጭ ላለነው ከሀገር ቤትም በተለየ በጣም ትልቅ ነው። ምክንያቱም ሰዎች ዝቅ ሲያደርጉን የመልስ ምት የምንሰጥበት፣ ማንነታችንን የምንገልፅበት፣ የበታችነት ሲመጣብን መከታ የምናደርግበት ነው።ዶ/ር እማዬነሽ ስዩም
አድዋ ኢትዮጵያዊ አንድነት ነው።ወ/ት ገነት ማስረሻ
የአድዋ ድል በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ዋጋ የተከፈለልን፤ በማንነታችን እንድንቆም የተሰጠን ነው። በጣም የምንኮራበትና የምንመካበት በዓል ነው።ድምፃዊት ክሪስቲና መልካሙ
የአድዋ ድል ማስታወሻ ነው። ሀገራችን በአውሮፓውያን እንዳትገዛ ያደረጉልን አባቶቻችን መታሰቢያ ቀን ነው። የአድዋ ድል ስማችን እንኳ 'ከሪም' 'ተስፋዬ' እንዲሆን ያደረገ ቀን ነው። አለበለዚያ መጠሪያችን 'ማሪዮ' 'ማሪያ' ይሆን ነበር። ቋንቋዎቻችንም ይጠፉ ነበር።ዲጄና የመድረክ መሪ ከሪም ዲጋል
ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም፤ በታሪክም ነው። አድዋ ማንነታችን፣ የከፍታ ልዕልናችን ነው። አሁን በኢትዮጵያ የመጣብንን የመከፋፈል ሁኔታ የምናስወግድበት፤ ለልጆቻችን የአባቶቻቸውን ታሪክ የምናስረክብበት በዓል ነው።ድምፃዊ መሰንቆኛ 2Pac





