ዛሬ ሐሙስ ጥር 30 በተካሔደው 6ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባ ከፍተኛ መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነቶች ተሰጥተዋል።
በሥራ ኃላፊነት አሰጣጡም፤
- አቶ ተመስገን ጥሩነህ፤ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣
- አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣
- ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል።
ከተሿሚዎቹ ሁለቱ አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴና ዶ/ር መቅደስ ዳባ የገዢው ብልፅግና ፓርቲ አባላት እንዳልሆኑ ተነግሯል።

Newly appointed ministers Ambassador Taye Atseke Tselassie (L) and Dr Mekdes Daba (R). Credit: EPO
ይህንኑ አስመልክቶም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "የብልፅግና አባል ባይሆኑም አገርና ጥቅምን ባስቀደመ መልኩ የሚደረገው መተካካት ይቀጥላል" ብለዋል።
አቶ ተመስገን ጥሩነህና አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ኃላፊነቶችን ሊረከቡ የቻሉት በተሰናባቹ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ምትክ በመተካት ነው።

Outgoing Ethiopian Deputy Prime Minister and Foreign Minister Demeke Mekonnen. Credit: KENA BETANCUR/POOL/AFP via Getty Images