ሲድኒ የገበያ ማዕከል ውስጥ ከዘጠኝ ወር ሴት ልጇ ጋር በስለት የተወጋችው እናት ሕይወቷ አለፈ፤ ሕፃኗ እያገገመች ነው

ፖሊስ ስድስት ስዎችን በስለት የገደለውንና 12 ሰዎችን ያቆሰለውን ግለሰብ ማንነት ገልጧል።

Bondi.jpg

Residents begin to lay flowers at the scene of yesterday's mass stabbing at Bondi Junction in Sydney. Credit: AAP / Dean Lewins

ቅዳሜ ኤፕሪል 13 / ሚያዝያ 5 ከቀትር በኋላ ሲድኒ ቦንዳይ ጃንክሽን ዌስትፊልድ የገበያ ማዕከል በደረሰ የጩቤ ጥቃት ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውንና 12 ሰዎች በፅኑዕ መቁሰላቸውን የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፖሊስ አስታውቋል።

ሕይወታቸውን ካጡት ሰዎች ውስጥ አምስቱ ሴቶች ሲሆኑ አንደኛው ግለሰብ ወንድ መሆኑም ተገልጧል።

ለሞት ከተዳረጉት ውስጥ የ38 ዓመቷ አሽ ጉድ ራሷን ከመሳቷና ሕይወቷን ከማጣቷ በፊት በስለት የተወጋችውን የዘጠኝ ወር ልጇን አጠገቧ ለነበረ ለማታውቀው አንድ ገበያተኛ "እርዳልኝ - አደራ" ብላ ሰጥታለች።

ሕፃኒቱ በፅኑዕ የቆሰለች ቢሆንም እያገገመች መሆኑን ፖሊስ ገልጧል።

የስድስት ሰዎችን ሕይወት በስለት የነጠቀውና 12 ስዎችን ለፅኑ የመቁሰል አደጋ የዳረገው ግለሰብ በኩዊንስላንድ ብሪስበን አካባቢ ነዋሪ የነበረ የ40 ዓመት ሰው ሲሆን፤ ወደ ሲድኒ ከመጣ አንድ ወር ያህል እንደሆነና ስሙም ጆኢል ካውቺ መሆኑን ፖሊስ አያይዞ ይፋ አድርጓል።

የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት ውስጥ ሁለቱ አውስትራሊያ ውስጥ ዘመድ አዝማድ የሌላቸው እንደሆኑና ከመጡበት ሀገር ለሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ስለደረሰባቸው አደጋ መገለጡም ተነግሯል።

ፖሊስ የስለት ጥቃቱ ከርዕዮተ ዓለማዊ አተያይ፣ ሃይማኖትም ሆነ ሽብር ጋር የተገናኘ ሳይሆን ከአዕምሮ ሕመም ጋር የተገናኘ እንደሁ ገልጧል።

Share

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo, NACA
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service