Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

የአክሱም ሐውልት ዳግም ለጎብኚዎች ክፍት ተደረገ

በአክሱም ከተማና አካባቢው የሚገኙ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ጥንታዊ ቅርሶች ለቱሪስቶች ክፍት ተደርገዋል።

Axum.jpg

4th century King Ezana's Stela and fallen and broken Great Stele at the Northern Stelae Park in Axum, Tigray Region, Ethiopia. Credit: Arterra/Marica van der Meer/Universal Images Group via Getty Images

የአክሱም ሀውልት ዳግም ለጎብኚዎች ክፍት መደረጉን በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የጽሕፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ገብረመድህን ፍፁም ብርሀን ለኢዜአ እንዳስታወቁት፤ በአክሱም ከተማና አካባቢው የሚገኙ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ጥንታዊ ቅርሶች ለቱሪስቶች ክፍት ተደርገዋል።

ቅርሶቹ ዳግም ለጎብኚዎች ክፍት እንዲሆኑ ሕብረተሰቡ በጉልበቱ፣ በገንዘቡና በሙያው ያደረገው ተሳትፎ የላቀ እንደነበርም ተናግረዋል።

የቱሪዝሙን ዘርፍ ወደነበረበት ለመመለስና ሕብረተሰቡ ለቱሪስቶች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሳደግ ለፎቶ ግራፍ ባለሙያዎች፣ አስተርጓሚዎች፣ ለባህላዊ ጌጣጌጦችና ቅርፃቅርፅ ባለሙያዎች እንዲሁም ለባለ ሆቴሎች ስልጠና መሰጠቱን አስረድተዋል።

በአክሱምና አካባቢው የሚገኙ ቅርሶችና ሙዚየም ለጎብኚዎች ተደራሽ ለማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ክፍት መደረጋቸውን ገልጸዋል።

በአክሱምና አካባቢው የሚገኙ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ጥንታዊ ቅርሶች ለመጎብኘትና ለማየት በየአመቱ ከ30 ሺህ በላይ የውጭ ሃገር ቱሪስቶች ይጎበኙት እንደነበር አስታውሰዋል።

ጎብኝዎቹ በአክሱምና አካባቢ በሚኖራቸው ከ2 እስከ 3 ቀናት ቆይታ ከሚያገኙት አገልግሎት የቱሪዝም ጽህፈት ቤቱና ነዋሪው በዓመት ከ180 ሚልዮን ብር በላይ ገቢ ያገኝ እንደነበረም ጠቅሰዋል።


1 min read

Published

By Stringer Report

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now