ዕንቁጣጣሽን እያከበራችሁ ባላችሁበት ወቅት ልባዊ መልካም ምኞቴን አቀርባለሁ።
የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የለውጥና እና ተስፋ ወቅት ነው።
ከቤተሰብ እና ወዳጆች ጋር በጋራ ለመታደም፣ አንድ ላይ ስላሰባሰባችሁም ምስጋና ማቅረቢያና በብሩህ ተስፋ ተመልቶ ወደፊት ማማተሪያ ጊዜ ነው።
በመድብለ ባሕላዊት ሀገራችን ዋጋ እና ከበሬታ በተቸራቸው የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አስተዋፅዖዎች አውስትራሊያ በልፅጋለች።
ዕንቁጣጣሽ በተለምዷዊ አጠራር አውስትራሊያን ሀገራችን ብለው በሚጠሩቱ ሁሉ በበርካታ መንገዶች ሀገራችን የተጠናከረችበት መሆኑን ልብ የሚያሰኝ ብርቱና ልብን አሟቂ ሆኖ ግዘፍ የሚነሳ ነው።
ለሁላችሁም፤ አዲሱ ዓመት የደህንነትና የሐሴት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
ሰላም፣ ብልፅና እና ደስታን ለእናንትና ለዘመድ አዝማዶቻችሁ ሁሉ ይዞላችሁ ይምጣ።
አንቶኒ አልባኒዚ
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር
ሴፕቴምበር 2025