በቅንጅቱ ስም [የሊብራል - ናሽናልስ] የአውስትራሊያ ኢትዮያውያን ማኅበረሰብን መልካም አዲስ ዓመት ለማለት እሻለሁ።
ዕንቁጣጣሽ ከቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶች ጋር ለመታደም፣ ማዕድ ለመቋደስ፣ ላለፈው ዓመት ምስጋና ለማድረስና መጪውን ብሩህ ዘመን አሻግሮ ለመመልከት ልዩ ወቅት ነው።
ለአውስትራሊያ፤ ንቁ ለሆኑቱ ኢትዮጵያውያን መኖሪያ ሀገር መሆን መታደል ነው።
ከግማሽ ክፍለ ዘመን በፊት ከመጡት የመጀመሪያዎቹ ቤተሰቦች አንስቶ ቀጣይ የፍልሰት ታሪካችንን እስከተቀላቀሉቱ ድረስ።
የበለፀገ ባሕልን፣ ጥብቅ ቤተሰባዊነትን እና መፃዒ ጊዜያትን እዚህ ለመገንባት መንፈስን አነቃቂ ቁርጠኝነትን ይዛችሁ መጥታችኋል።
እናም ይህ ድንቅ ከተለያዩ በርካታ ዘውጌ ማኅበረሰባት፣ ቋንቋዎች፣ ሃይማኖቶችና ብዝኅነትን የተላበሱ ሆነው፤ ግና ሕብር በእጅጉ በሚያሻበት ወቅት ያብራሉ።
ዕንቁጣጣሽ ወዳጅነትና ክብር በተመላበት መልኩ ሁሉንም የማሰባሰቢያ ጊዜ ነው።
በመላ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አነስተኛ ንግዶችን በማካሔድ፣ በጥናት ዘልቆ በመሔድ፣ በስፖርት፣ በጤና ክብካቤና ትምህርት ዘርፍ ተሠማርተው በመሥራት አስተዋፅዖዎችን አበርክተዋል።
ሲልም፤ ታሪካችሁን፣ ሙዚቃዎቻችሁንና ልማዶቻችሁን አጋርታችኋል።
እናንት ሀገራችን በመልካም የምትቀበለው ብዝኅነትና ሙሉዕ መልካም ዕድሎች ጠቃሚ አካል ናችሁ።
በጋራ ለመፀለይ፣ ለክብረ በዓል ለመታደምና በጋራ ለማክበር በምትሰባሰቡበት ወቅት፤ እኛም ከጎናችሁ ሆነን እንደምናከብረው እባካችሁን ዕወቁልን።
የእናንተ ስኬት የአውስትራሊያ ስኬት ነው፤ የእናንተ መጪ ጊዜ እንደ ሀገር በጋራ የምንጋራው መጪ ጊዜ ነው።
ለሁላችሁም መልካም አዲስ ዓመት!