Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

"ሼክስፒር እኔ ኮርዴሊያን ሆኜ ስጫወት ቢያየኝ፤ እርግጠኛ ነኝ፤ ጥቁር ሴት በመሆኔ ይደነግጣል። በእሱ ጊዜ ዘረኛነት በጣም ነበር።" ተዋናይት አሁንም አበበ

Ahunim Cordelia II.png
Actress Ahunim Abebe is performing at Shakespeare's King Lear play as Cordelia, one of the King's three daughters. Credit: Brett Boardman

ተዋናይት አሁንም አበበ ከኖቬምበር 15 አንስቶ ሲድኒ በትወና ላይ ያለውና ጃኑዋሪ 4 የሚያከትመው የሼክስፒር King Lear ተውኔት ኮርዴሊያን ብቻ አይደለችም። ከተውኔት ባሻገር ስላላት የማኅበራዊ ፍትሕና የተፈጥሮ ክብካቤ አንቂነት ሕይወቷ፣ የሼክስፒር ተውኔቶች ዘመን ተሻጋሪነትና አሁንም ድረስ ገነን ሆኖ የቆየበትን አስባብ አንስታ አተያይዋን ታጋራለች።

Published

Updated

By Kassahun Negewo

Source: SBS

Share this with family and friends

ተዋናይት አሁንም አበበ ከኖቬምበር 15 አንስቶ ሲድኒ በትወና ላይ ያለውና ጃኑዋሪ 4 የሚያከትመው የሼክስፒር King Lear ተውኔት ኮርዴሊያን ብቻ አይደለችም። ከተውኔት ባሻገር ስላላት የማኅበራዊ ፍትሕና የተፈጥሮ ክብካቤ አንቂነት ሕይወቷ፣ የሼክስፒር ተውኔቶች ዘመን ተሻጋሪነትና አሁንም ድረስ ገነን ሆኖ የቆየበትን አስባብ አንስታ አተያይዋን ታጋራለች።

አንኳሮች

  • ሼክስፒርና አሁንም
  • የጥበብ ሰዎች የሀገር ኅሊናነት
  • ተልዕኮዎችና ተግዳሮቶች
የእኔ ትውልድ ዝም ብሎ አይቀመጥም። ለውጥ ለማምጣት እንሰባሰባለን፣ እንደራጃለን፣ ሠልፍ እንወጣለን፣ ተቃውሞ እናሰማለን፣ በኑሮ ላይ ለውጥ ለማምጣት እንሞክራለን፤ መንግሥትን challenge እናደርጋለን።
ተዋናይት አሁንም አበበ
የአርቲስት ሥራ ጊዜውን ማሳየት ነው። ሕዝብ እራሱን እንዲጠይቅ ማድረግ ነው። ለentertainment እና ለቁንጅና አይደለም። እኔ የማስበው እንደዚያ ነው።
ተዋናይት አሁንም አበበ
ኢትዮጵያዊ - ሀበሻ በመሆን አንድ ነገር ለስኬት ስናበቃ፤ ሁላችንም ሕልማችንን ለስኬት እናበቃለን። ከየትም ብንሆን፤ ኢትዮጵያዊ፣ ኤርትራዊ፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግራይ አንድ ነን።
ተዋናይት አሁንም አበበ

Latest podcast episodes

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now