"ወጣት ሴቶች ውስጣቸው ጥንካሬና ችሎታ እንዲኖራቸው ነው የምፈልገው፤ ለውጥ ቢኖርም አሁንም ወንዶችና ሴቶች ገና እኩል አይደሉም" ተዋናይት አሁንም አበበ

Cordelia Ahunm Abebe I.png

Actress Ahunim Abebe is performing at Shakespeare's King Lear play as Cordelia, one of the King's three daughters. Credit: Brett Boardman

ተዋናይት አሁንም አበበ ከኖቬምበር 15 አንስቶ ጃኑዋሪ 4 ለማብቃት መድረክ ላይ ለቲአትር አፍቃሪዎች እየተተወነ ባለው የሼክስፒር King Lear ተውኔት የኮርዴሊያን ገፀባሕሪ ተላብሳ በመተወን ላይ ናት። ከስሟ ስያሜ እስከ ተውኔት ሕይወቷ ታወጋለች። አውስትራሊያ ተወልዳ ብታድግም፤ አማርኛዋ የጠራ ነው።


አንኳሮች
  • ውልደትና ዕድገት
  • የሀገር ቤት ትውስታዎች
  • የአያት ውርሰ ዕሴቶች
  • አሁንም እና ኮርዴሊያ
  • የ1605 / 6ቷ እና የ2025ቷ ኮርዴሊያ
አያቴ ለሰው የምትመክረውን እራሷ የምታደርግ ነበረች። Hypocrite አልነበረችም።
ተዋናይት አሁንም አበበ
አሁን በምንኖርበት ዓለም እውነትን ማግኘት ከባድ ነው። ብዙዎች እውነት አይናገሩም፤ እውነቱን ይደብቃሉ።
ተዋናይት አሁንም አበበ
ኮርዴሊያ [የንጉሥ ሊር ሴት ልጅ] በአሁኑ ወቅት ብትኖር ማኅበራዊ ሚዲያ አይኖራትም ነበር። ብዙ መጽሐፍ ይኖራታል እንጂ። ምክንያቱም፤ ብዙ ሶሻል ሚዲያ ያላቸው ሰዎች ቶሎ ስሜታዊ ይሆናሉ፣ ቁጡ ይሆናሉ፣ ነገሮችንም ቶሎ ይረሳሉ። በሶሻል ሚዲያ ብዙ ማንበብ፣ መመራመር፣ እራስን ማወቅ አያስፈልግምና፤ Headlines [ርዕሰ ዜናዎችን] በማየት ብቻ ብዙ ያወቁ ይመስላቸዋል።
ተዋናይት አሁንም አበበ

Share

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now