በፌዴራል ሌበር ስም ለሁላችሁም መልካም አዲስ ዓመትን ልመኝ እወዳለሁ።
ወረርሽኙ ለእያንዳንዱ የአውስትራሊያ ማኅበረሰብ በእጅጉ ፈታኝ ነው።
በተለይም ከበርካታ ቤተሰቦቻቸውና ጓደኞቻቸው ተለይተው ላሉቱ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ። ምንም ጥርጣሬ የለውም፤ አገር ቤት ካለው ብርቱ አዋኪ ሁነት ጋር።
ይሁንና ይህ አዲስ ዓመት ለሁላችንም ሐሴትን እንደሚያጎናፅፈን ጥርጣሬ የለኝም።
ሁኔታው ሲፈቅድም አብሬያችሁ ለማክበር እሻለሁ።