አንኳሮች
- የብዙኅን መገናኛና ማኅበራዊ ሚዲያ አሉታዊ የጦርነት አስተዋፅዖዎች
- ሥነ ልቦናዊ ጫናዎች
- ሕፃናትን ድገፋ
- ጦርነትና ስዕል
- አማራጭ መንገዶች
ሥነ ምግባር የጎደላቸው የሚዲያ አካላት አንዳንድ ነገሮችን በማጋነን በሀገር ቤት ያለ ቤተሰብን፣ ሌሎች አካባቢ ያሉ አካላትን መረበሹ ነው እኛን እየረበሸ ያለው እንጂ የኳታር መንግሥት ማድረግ የሚገባውን ክብካቤ እያደረገ፤ በኑሮ ውድነት ላይ አንዳችም ጭማሪ የለብንም። የነዳጅ ጭማሪ አልተደረገም። ትልቅ ድጋፍ እያደረገልን ነው የምንገኘው።ሰዓሊ ተሰማ ተምትሜ አሥራቴ
ቤተክርስቲያንን ጨምሮ የማኅበራዊና ሕዝባዊ መሰባሰቦች መቶ በመቶ ታግደዋል። ያም ለደኅንነት ሲባል ነው። ሆኖም ሕፃናትና የቤተሰብ አባላት ላይ የፈጠረው ጫና ይኼ ነው አይባልም። ሥራም ላይ እያለን መጠነኛ የመረበሽ ስሜት ይኖራል።ሰዓሊ ተሰማ ተምትሜ አሥራቴ
ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ የሀገሪቱን ሕግና ሥርዓት በመጠበቅ ከ10 እስከ 40 ኪሎ ሜትሮች እየተጓዝኩ 14 ቤተሰቦች ያሉበት ድረስ ሔጄ ጎብኝቻለሁ። ስዕል ባለው ትልቅ አቅም ልጆችን በማዝናናት የሥነ ልቦና ድጋፍ ለማድረግ።ሰዓሊ ተሰማ ተምትሜ አሥራቴ





