ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

ቤንዴሬ ኦቦያ፤ ኢትዮጵያዊቷ የአውስትራሊያ ብሩህ ኮከብ አትሌት

ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Community

Australian athlete Bendere Oboya.


Published 22 June 2022 at 6:18pm
By Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

ቢንዴሬ ኦቦያ ውልደቷ እ.አ.አ በ2000 ዓ.ም ጋምቤላ ከተማ ኢትዮጵያ ነው። የአባቷን ኦፓሞ ኦቦያ ኦጋሬን እግር ተከትላ ለአገረ ኬንያ የስደት ሕይወት ግድ የተሰኘችው የአንደኛ ዓመት የልደት በዓል ሻማዋን 'እፍ' ብላ ባጠፋች ማግስት ነው። ዕድገቷ ምዕራብ ሲድኒ ፔንዲል ሂል ክፍለ ከተማ ሲሆን፤ ኑሮዋን ሜልበርን ከተማ ካደረገች ከርማለች። ኢትዮጵያዊ ደሟ አጋዥ ሆኗት ከታዳጊ ወጣቶች የክፍለ ከተማ የሩጫ ውድድር እስከ ቶኪዮ ኦሎምፒክ ደርሳለች። የSBS ቴሌቪዥን የሕይወት ታሪኳን RUNGIRL በሚል ዘጋቢ ፊልም ቀርፆ ኦገስት 18 / ነሐሴ 12 በአውስትራሊያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 8:30pm ለሕዝብ ዕይታ ሊያቀርበው መሰናዶውን ጨርሷል።


Published 22 June 2022 at 6:18pm
By Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS


አንኳሮች


 

Advertisement
  • ውልደትና ዕድገት
  • የስደት ሕይወት
  • ቤንዴሬና የአትሌቲክስ ዓለም

Share