ምዕራብ አውስትራሊያውያኑ ኢትዮጵያዊትና ኤርትራዊ ተጋቢ ሙሽሮች የሠርጋቸውን ወጪ ለኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች ለገሱ

Bizualem (Lili) Tegene and Daniel Bahta. Source: Tegene and Bahta
ኢትዮጵያዊቷ ሙሽሪት ብዙዓለም (ሊሊ) ተገኔ እና ኤርትራዊው ሙሽራ ዳንኤል ባህታ የሠርግ ወጪያቸውን ለኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች እንዲደርስላቸው በፐርዝ ምዕራብ አውስትራሊያ ልዩ የመስቀል በዓል ዝግጅት ላይ ቸረዋል። ሙሽሪት ሊሊ "ኢትዮጵያ አገራችን በተለያዩ ችግሮችና ረሃብ ውስጥ ባለችበት ወቅት የምንደርስላት እኛ ነን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን በቃሽ እንዲላትና ጋብቻንንም እንዲባርክልን በፀሎታችሁ አስቡን" ስትል፤ ሙሽራ ዳንኤል ባህታ "ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን አንድ ነን፤ ችግሩ የጋራችን ነው" ብሏል።
Share