"የጥምቀትን የተለያዩ የሃይማኖት ሥርዓቶችንና የሕዝቡን ደስታ ስመለከት ሀገሬ ኢትዮጵያ ያለሁ ነው የመሰለኝ" መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ

Epiphany at Footscray.png

Celebration of Epiphany in Melbourne, Australia. Credit: Sentayehu Bekele

የከተራና ጥምቀት በዓል በሀገረ አውስትራሊያ የሜልበርንና ፐርዝ ከተሞች ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ እmንት ተከታዮች ዘንድ ደምቆና ገንኖ ተከብሮ ውሏል። በዓለ ጥምቀቱን በጋራ የአንድነት መንፈስ ያከበሩት ቤተክርስቲያናት፣ ምዕመናንና ምዕመናት የእምነትና ሀገራዊ አንድነትን አንፀባርቀዋል። የሃይማኖት አባቶችና ታዳሚዎች አተያያቸውን አጋርተውናል።


አንኳሮች
  • በዓለ ጥምቀት
  • ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች
  • የበዓለ ጥምቀት ተምሳሌነት
  • ሃይማኖታዊ ፋይዳዎች
  • በረከተ ተሳትፎ
የጥምቀት በዓል ታላቅ በዓል ነው፤ ታሪካዊ በዓል ነው።
የሜልበርን መካነ ሰላም ልደታ ለማርያም ወገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ፅዮን ቀሲስ እንግዳ ቸሩ
የጥምቀት በዓል የፍቅር በዓል ነው። በዓሉ በየዓመቱ በምዕመናኑ ተሳትፎ እያደገ እየሔደ ነው። ሰውና እግዚአብሔር አንድነታቸው የተጠበቀበት በዓል ነው። የጥምቀት ምስጢር ወደ ቤተ ክርስቲያን የመግቢያ በር ነው።
በሜልበርን ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ቀሲስ ስንታየሁ አባተ
ጥምቀት ሃይማኖት ብቻ አይደለም፤ አይለይም። እንደ ጨዋ ሆኜ ሳየው፤ እንደ ሀገር አምባሳደርነት ነው። ምንም እንኳ ከሀገራችን ብንለይም፤ ሃይማኖታችንንና ባሕላችንን ሳንለቅ ለልጆች መተላለፉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንንና የኢትዮጵያን ቀጣይ መሆን ነው የሚያሳየው።"
አቶ እሸቱ ሙሉጌታ፤ የሜልበርን ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያንና የሰበካ ጉባኤ አባል
የጥምቀት በዓልን በአማረ ሁኔታ እንዲደምቅ ላደረጉ የበዓሉ ዝግጅት ኮሚቴ አባላት፣ የሰበካ ጉባኤ አባላትንና የሜልበርንን ሕዝብ ሁሉ ላመሰግን እወዳለሁ።
አቶ ኢሳያስ መለስ፤ የሜልበርን መካነ ሰላም ቅድስተ ልደታ ለማሪያም ወገብርኤል የሰበካ ጉባኤ አባል
የጥምቀት በዓል በፐርዝ ከተማ በጣም አስደናቂ ነው። ሶስት ዐቢያተ ክርስቲያናት ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ አማኑኤልና ደብረ መድኃኒት መድኃኒዓለም የአባቶችን ሥርዓት ተከትለው አንድ ላይ አክብረዋል።
መልአከ ምህረት መምህር ዜናዊ፤ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል - ኪዳነ ምህረት አስተዳዳሪ፣ የምዕራብ አውስትራሊያ የትምህርትና ስብከት የትምህርት ኃላፊ

Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service