ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን፤ በኦስቲን ኮሙዩኒቲ ኮሌጅ ጂ አይ ኤስ ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ ሰሞኑን "ከፑንት እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ፤ በካሳሁን ሰቦቃ በSBS የተደረጉ ቃለ መጠይቆችና መጣጥፎች" በሚል ርዕስ በዶ/ር ግርማ አውግቸው አርታኢነትና በሴማዊ ጥናቶች መካነ ተቋም አሳታሚነት ለሕትመት በበቃው መፅሐፍ ላይ "የኢትዮጵያ ታሪካዊ የመዲናዎች ዝውውር ጂኦግራፊያዊ ጠባያት" በሚል ርዕሰ መጠሪያ ስላቀረቡት የመጣጥፋቸው ጭብጦች ይናገራሉ።
አንኳሮች
- የመዲናዎች ዝውውር ታሪካዊ ዳራና ዋነኛ አስባቦች
- የመዲናዎች ዝውውር፤ ከምጣኔ ሀብት፣ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ብሔራዊ ማንነት ግንባታ አንፃር
- የአዲስ አበባ አስተዳደር አወዛጋቢ አተያዮች
ትግራይን በአመዛኙ የትግራይ ተወላጆች ነበሩ የሚያስተዳድሯትና፤ የብሔር ብሔረሰብ ጭቆና ትግራይ ውስጥ ያልሠራ እንደሆነ ይታወቃል።ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን
Share






