"ጥምቀት ከፍተኛ የሆነ ምስጢር ያለው፣ የስላሴ ሶስትነት፣ አንድነት የተገለፀበት፤ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር የተወለደበት ሙሉ የሆነበት ነው" ቀሲስ መንግሥቱ ኃይሉ

W &K.png

Woknek Bayeh (L) River city at dusk and rainbow Brisbane (C) and Kesis Melake Tsehay Mengistu Hailu (R). Credit: Andrew Merry / Getty Images

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዓመታዊው በዓለ ጥምቀት በሀገረ አውስትራሊያ - ብሪስበን ከተማ በ Oxley Creek Common ከጃኑዋሪ 24 - 25 / ጥር 16 - 17 ተከብሮ ይውላል። ቀሲስ መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሉ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና በብሪስበን የደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ እንዲሁም አቶ ወርቅነህ ባየህ፤ በብሪስበን የደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ስለ በዓሉ መሰናዶ፣ መርሃግብርና የበዓለ ጥምቀትን ተምሳሌነትና ፋይዳዎች ያስረዳሉ።


አንኳሮች
  • በዓለ ጥምቀት በብሪስበን
  • ማኅበራዊ ፋይዳዎች
  • መንፈሳዊና ማኅበረሰባዊ አንድነት
  • የበዓል ከበሬታ ጥሪ
ጥምቀት ከኢትዮጵያዊ በዓልነት አልፎ ወደ ዓለም አቀፋዊ በዓልነት አድጓል። ይህ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያናችንም፣ ለሀገራችንም ትልቅ አንድምታ ያለው ነው።
ቀሲስ መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሉ
ጥምቀት በብዙ ሀገሮች ይከበራል፤ ነገር ግን እንደ ኢትዮጵያ ደምቆ የሚከበርበት፣ ባሕር ወርዶ አድሮ የሚከበርበት፣ ታቦታቱ ወርደው፣ ወንዝ አድረው ፤ ካህናቱ፣ ጳጳሳቱ፣ እላይ ቅዱስ ፓትሪያርኩ ድረስ ወርደው አክብረው፣ ባርከው የሚመለሱበት ሁኔታ የለም። ይህ ነገር ብዙዎችን እያስገረመ፣ ብዙዎችን እየማረከ፣ ብዙዎች ወደ እዚያ እንዲሔዱ እያነሳሳ ለሀገሪቱም ትልቅ ጥቅም ያመጣል። ለቤተ ክርስቲያኒቱም ትልቅ ሀብት ነው።
ቀሲስ መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሉ
ዘንድሮ ብሪስበን ውስጥ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንና የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ አብረው ሆነው ነው በዓሉን የሚያሳልፉት። ጥሩ በዓል እንደምናሳልፍ ምንም ጥርጥር የለውም።
ቀሲስ መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሉ
የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ወደ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እየሔዱ፤ የቅዱስ ገብርኤልም ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ እየመጡ መንፈሳዊ አገልግሎቱን ሊካፈሉ የሚችሉበት ትልቅ መድረክ ነው የተከፈተው። ወደ ፍቅር፣ ወደ ጥሩ መንገድ እያመራን ነው።
አቶ ወርቅነህ ባየህ
ዘንድሮ ሁለት ነን። አንድ አዲስ የተተከለ ቤተ ክርስቲያን አለ፤ ቅዱስ ሚካኤል። በቀጣዩ ዓመት እሱንም ይዘን አብረን እንወጣለን።
ቀሲስ መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሉ

Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service