አንኳሮች
- በፌዴራል የፀረ - መድልዖ ሕግ ሃይማኖትን ብቻ መሠረት ያደረገ መድልዖ ሕገ ወጥ ይደለም፤ በክፍለ አገራትና ግዛቶች ኝ አሕገ ወጥ ሊሆን ይችላል።
- የሥራ ፍትሕ ኮሚሽን፣ የአውስትራሊያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የአካባቢ ፀረ መድልዖ አካላት፤ ከፍርድ ቤት ውጪ የሃይማኖት መድልዖን አስመልክቶ ቅሬታን የማቅረቢያ መድረኮች ናችው
- በተወሰነ መልኩ ሕጋዊነትን የተላበሱ ጉዳዮች ሠራተኞች ሃይማኖታቸውን እንዳይተገብሩ እገዳ የሚያስጥልባቸው ሁኔቶች ይኖራሉ።
አውስትራሊያ ውስጥ፤ ሃይማኖታዊ ጥበቃዎችን አስመልክቶ ወጥ ሕግ የለም፤ ላለፉት ዓመታት ሃይማኖታዊ መድልዖ ድንጋጌን ለማሳለፍ ሂደቶች ተካሂደዋል።
ከሠራተኛ አኳያ፤ ሃይማኖትን መሠረት ካደረገ መድልዖ ለመከላከል የ ፍትሐዊ ሥራ አንቀፅ 2009 ን የተመረኮዙ አገር አቀፍ የሆኑ ጥበቃዎች አሉ፤ ይሁንና መጠነ ሽፋናቸው ውስን ነው።
ካሪና ኦኮቴል፤ በአውስትራሊያ መዲና ግዛት ብሔራዊ የማኅበረሰብ የሕግ ማዕከል ዘራዊና ሃይማኖታዊ መድልዖ ሕጋዊ አገልግሎት ገዲብ የሕግ ባለሙያ ናቸው።
አንድ ሃይማኖታዊ መድልዖ የደረሰበት ሠራተኛ ጉዳዩ በአንቀፁ መሠረት ለቅሬታ ስሚ ብቁ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት አስቀድሞ ማነጋገር የሚገባው የሥራ ፍትሕ ኮሚሽንን እንደሆነ ሲያመላክቱ፤
“ግብር ላይ የሚውል ውሳኔን ማሳለፍ ይችላሉ። ይሁንና ለፍትሕ ሥራ ኮሚሽን የሚቀርቡት ቅሬታዎች መጠን በቅጡ የተተረጎሙና በዙሪያቸውም ውስንነት አሏቸው” ብለዋል።

ለምሳሌ፤ አሠሪዎች የሥራ አመልካቾች ላይ በሃይማኖታቸው ሳቢያ አሉታዊ ተግባራትን ቢፈፅሙ ያ ሕገ ወጥ ተግባር ነው።
“በቀጠራ ወቅት መድልዖ ይከሰታል። ይሁንና ማረጋገጫ ለማቅረብ በእጅጉ አዋኪ ነው፤ መነሻው አስተውሎትን ያልተመረኮዘ የአንድ ጎን ወገንተኝነት ነው” ይላሉ ወ/ሮ ኦኮቴል።
በሥራ ፍትሕ አንቀጽ ያልተሸፈነ፤ በሥራ ባልደረቦች መካከል የሚከሰት ሃይማኖታዊ መድልዖን ያካተተም ሊሆን ይችላል።
በፌዴራል ደረጃ፤ ቅሬታዎች ዕልባት እንዲያገኙ መምሪያን የመስጠትና አሳሪ ያልሆኑ ምክረ ሃሳቦችን የመቸር ስልጣን ላለው የአውስትራሊያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሊቀርቡ ይችላሉ።
ወ/ሮ ኦኮቴል፤ በአብዛኛው ቅሬታዎችን ተከትሎ መልካም ስምን የማጉደፍና የሚዲያ ተጋላጭነት አሠሪዎችን ከቅሬታ አቅራቢዎች ጋር ከስምምነት ዕልባት ላይ እንዲደርሱ ያነሳሳቸዋል።
“እናም፤ ሰዎች ወደ ፍርድ ቤት ሳይሔዱ እርዳታና እልባት እንዲያገኙ ቅሬታዎቻቸውን በቀጥታ ለሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ቢልኩ፤ በጣሙን ፍሬያማ ይሆናል” በማለትም ወ/ሮ ኦኮቴል ይመክራሉ።
በክፍለ አገርና ግዛቶች ደረጃ፤ ሃይማኖታዊ እምነቶች ወይም እንቅስቃሴዎች በበርካታ አካባቢዎች በፀረ መድልዖ ሕጎች የተጠበቁ ናቸው። ይሁንና፤ ጥበቃዎቹ እንደሚኖሩበት አካባቢ የተለያዩ ናቸው።
የቪክቶሪያ የእኩል ዕድሎችና ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሕግ መምሪያ ዋና ኃላፊ የሆኑት ኤሚ ኮፐር፤ የሥራ ቦታ የሃይማኖት መድልዖን በተመለከተ ምሳሌዎችን ይሰጣሉ።

“አንዲት ይሁዲ ሴት በየሳምንቱ ቅዳሜ ለሻባት ስትል ሥራ ላይ መገኘት እንደማትችል በመግለጧ በአሠሪዋ አዋኪ ተብላ ተፈርጃለች። አንድ የሲክህ ሰው […] የሥራ ኃላፊው ራሱ ላይ የጠመጠመውን ተርባን እንዲያወልቅ አጠንክሮ ሲነገረው ጣጣ እንደገጠመውና መልካም ተቀባይነት እንደሌለው ተሰምቶታል። እንዲሁም፤ አንዲት ሙስሊም ሴት በእምነቷ መሠረት ለጥቂት ደቂቃዎች ትፀልይ ስለነበር፤የሥራ ባልደረቦችዋ እንደምን ቀኑን ሙሉ ትንሺዪቱ ዕረፍት ሲሏት ሰምታቸዋለች” ሲሉ ወ/ሮ ኩፐር ተናግረዋል።
እንደ የእኩል ዕድልና ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሁሉ የክፍለ አገራትና ግዛቶች አካላትም በፍርድ ቤት አማራጭነት ሁለቱም ቅሬታ አቅራቢዎችና ቅሬታ የሚቀርብባቸው ወገኖች ከጋራ ስምምነት ላይ የሚደርሱበትን እገዛ ያደርጋሉ።
ወ/ሮ ኩፐር በማያያዝም “ይቅርታ ማለት፣ የፖሊሲ ወይም የመመሪያ ለውጦችን ማድረግ፣ ግለሰብን መልሶ ወደ ሥራ ገበታው እንዲመለስ በማድረግ ለሠራተኞች ስልጠናን የመስጠት ወይም የገንዘብ ካሣ መክፈል ሊሆን ይችላል” በማለት አስረድተዋል።
በተወሰኑ ሁኔታዎች፣ አንድ ሠራተኛ ላይ ሃይማኖትን አካትቶ መድልዖን ማድረግ ሕገ ወጥነት አይሆንም።
ለምሳሌ ያህል፤ ቪክቶሪያ ውስጥ፤ ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ ድርጅቶች ሠራተኛን በመቅጠር ረገድ የተወሰኑ መድልዖን ሊያደርጉ ይችላሉ።

“ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ መልኩ የተወሰነ አሥፈላጊ የሥራ አካልን መስጠት፣ ግለሰቡ የሃይማኖታቸውን መመዘኛዎች እንደማያሟላ ማስታወቁ፤ ምክንያታዊነትና ተመጣጣኝነት ያለው ነው” ሲሉ ወ/ሮ ኩፐር ያክላሉ።
የብላክቤይ የሕግ ባለሙያዎች የንግድ አለመስማማቶች ሽርካ የሆኑት ጀስቲን ካሮል፤ በሥራ ፍትሕ ድንጋጌ መሠረት የሃይማኖት ተቋማት የመድልዖ ድርጊት የሚፈፅሙት ሕገወጥ በሆነ መልኩ ሳይሆን "በቅን ዕሳቤ" ወይም "ከሃይማኖታዊ ተጋላጭነት ወይም የእምነት መርህ ጋር የተያይዘ ጉዳትን" ለማስወገድ ሲሉ እንደሁ ያስረዳሉ።
በሥራ ፍትሕ ድንጋጌ፣ የክፍለ አገርና ግዛት ሕጎች መሠረት ግዴታዎቻቸውን በመፈፀም ሙግትን ወይም ቅሬታዎችን ማስወገድ የአሠሪዎች ኃላፊነት መሆኑን አቶ ካሮል ይናገራሉ።
ይሁንና፤ አሠሪዎች ሁኔታቸውን የሚቆጣጥሩባቸው ደረጃዎች እንዳሉ ሲያመላክቱም፤
“ንግዳቸውን በማካሔዱ ረገድ ሃይማኖታዊ ምልከታ ያላቸውን ሰዎች፤ እርግጥ ነው፤ ሌሎች የእምነት ተከታይ ያልሆኑ ሰዎች ላይ ሃይማኖታዊ ጣልቃ ገብነት በማያደርጉ ወይም ከቶውንም በማይገቡበት መልኩ ማካተቱን መሞከር" እንደሚችሉ ያመላክታሉ።

“እንዲሁም፤ ግልፅ መሆን፣ ሠራተኞች ምን እንደሚጠበቅባቸው በቀጥታ መንገር ምን መጠበቅ እንዳለባቸው እንዲገነዘቡ ይረዳል” ሲሉም አተያያቸውን ያጋራሉ።
ወ/ሮ ኦክቶቴልም በበኩላቸው፤ የሃይማኖት መብቶችን በሥራ ገበታ ላይ መጣስን በተመለከተ፣ ክስተቶቹ ሁሌም ቀጥተኛ አይደሉምና ከዘር መድልዖ ወይም ከሌላ ሕጋዊ ካልሆኑ ጥሰቶች ጋር ሊዛነቁ እንደሚችሉ ይናገራሉ።
አያይዘውም “አንድ ደንበኛ አለን፤ ለምሳሌ ያህል፤ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ሊወስድ የሚሻ ሆኖም ያን ለማድረግ በቂ ሁኔታዎች የሉም። እንዲያም ሆኖ ምናልባትም የገመና ቅሬታ ሊኖራቸው እንደሚችል መለየት መቻል አለብን።
“እናም፤ የሕግ ምክር ለሚጠይቁ ሰዎች በጣሙን ጠቃሚ ነው፤ ስለምን የሕግ ባለሙያው የተለያዩ አማራጮችን በመዳሰስ፤ የሕጉ ውስንነት እንዳለ ሆኖ የተሻል እርምጃ የሚወሰድበትን መንገድ ሊያመላክት ይቻለዋል” በማለት ወ/ሮ ኦኮቴል ያጠቃልላሉ።
በክፍለ አገር / ግዛት ደረጃ የሃይማኖት መድልዖ ቅሬታን ለማቅረብ መረጃን ካሹ እኒህን ድረገፆች ይጎብኙ፤
| ACT | ACT Human Rights Commission | https://hrc.act.gov.au/ |
| NSW | Anti-Discrimination Board of NSW | https://antidiscrimination.nsw.gov.au |
| NT | Northern Territory Anti-Discrimination Commission | http://www.adc.nt.gov.au/ |
| QLD | Queensland Human Rights Commission | https://www.qhrc.qld.gov.au/ |
| SA | South Australian Equal Opportunity Commission | https://eoc.sa.gov.au/ |
| TAS | Equal Opportunity Tasmania | https://equalopportunity.tas.gov.au/ |
| VIC | Victorian Equal Opportunity & Human Rights Commission | https://www.humanrightscommission.vic.gov.au/ |
| WA | Western Australian Equal Opportunity Commission | http://www.eoc.wa.gov.au/ |








