አንኳሮች
- ከጎንደር እስከ አውስትራሊያ
- ከሕክምና ወደ የውበት ሳሎን
- ሕልፈተ ሕይወትና ስንብት
- ምስጋና
እናታችን ሀገሯን በጣም ትወዳለች። በጣም መልካም ሰው ነበረች። 'ነበረች' የሚለውን ቃል መቀበል እየከበደኝ ነው የምለው።የወ/ሮ ዕሌኒ ብርሃኑ ሴት ልጅ ሊዲያ ዓለማየሁ
ዕሌኒ ለእኔ አራተኛ እህቴ ናት። በጣም ሀገር ወዳድና ጥሩ ሰው ናት። በጣም ጨዋ፣ ሃይማኖተኛ፣ የሥራ ሰው ናት። ከቤተሰብ ውጪ የብዙ ሰው ጉሮሮ የምዘጋ ናት። ለእኔ እህቴ ብቻ አይደለችም። እናቴም፤ አማካሪዬም ናት።ወ/ሮ ፍቅርተ ብርሃኑ
ለብዙ ዓመታት ተራርቀን ነው እንኖር የነበረው። የእናትን ፍቅር እንኳ በቅጡ አናውቅም ነበር። እዚህ መጥተን እናሳርፋታለን ብለን የተፈጠረውን ነገር እስካሁን ማመን አልችልም።የወ/ሮ ዕሌኒ ብርሃኑ ወንድ ልጅ ማቲያስ ዓለማየሁ
ዕሌኒን የማውቃት ከ20 ዓመታት በላይ ነው። ትህትናዋ፣ መስተንግዶዋ፣ አመለካከትዋ፣ ረጋ ያለች፣ ጨዋና አስተዋይ ነች። ደከመኝ፣ ሰለቸኝ የማትል፤ ለሰው ያላት ፍቅር፣ ርህራሔዋ ይኽ ነው ተብሎ አይገለፅም። ለልጆቿ ጣሪ፣ ጋሪ የሆነች እናት ነች። የደረሰባት አደጋ አይደለም በዕውን፤ በሕልምም የሚታሰብ አይደለም። በጣም ልብ የሚነካ ነው፤ በጣም ጥልቅ ሐዘን ነው የተሰማኝ።አቶ ተስፋዬ ሙሉጌታ የወ/ሮ ዕሌኒ ብርሃኑ ታላቅ እህት ባለቤት
ዕሌኒ ብሩህ አዕምሮ ያላት፣ በጣም ቀልጣፋ፣ በጣም ሳቂታ፣ በጣም ደግ፣ በጣም ተግባቢ ሰው ነች። ይህን ደግሞ ብዙ ሰው የሚመሰክርላት ናት። በአሟሟቷ በጣም ነው ያዘንኩት።አቶ ወንድም አገኝ አዲስ የወ/ሮ ዕሌኒ ቤተሰብ የቅርብ ወዳጅ












